ዶ/ር አክሊሉ የሳዑዲ የንግድ ልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ኃይለሚካኤ የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የልዑካን ቡድኑ በግብርና ዘርፍና በእንስሳ እርባታ ላይ ኢንቨሰት ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እስከአሁን ሁለት ቦታዎችን የጎበኘ ሲሆን፥ አንደኛው በኢትዮ-ጅቡቲ ድንበር ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዶክተር አክሊሉ በሁለቱ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ማሰባቸውን አበረታተዋል፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ ከግብርና ጋር የተያያዙ አሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት ለመላክ ጽኑ ፍላጎት እንዳላትም ገልጸዋል፡፡

ይህም የስራ እድልን ከመቅረፍ አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አንስተው፥ ለልዑካን ቡድኑ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸውም አስታውቀዋል፡፡