በግንቦት ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግንቦት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በግንቦት ወር፥ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎቹ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በአዲስ አበባ በሚያዚያ ወር ሲሸጥበት ከነበረው 22 ብር ከ93 ሳንቲም፥ በግንቦት ወር በ1 ብር ከ41 ሳንቲም ጭማሪ በማድረግ 23 ብር ከ80 ሳንቲም እንደሚሸጥም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዓለም አቀፍ ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግም እንደ አስፈላጊነቱ የዋጋ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቁሟል።