የኢትዮጵያ አየር መንገድና የሳዑዲ አረቢያው ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ የጥገና ስራን በትብብር ለማከናወን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቴክኒክ ክፍል ከሳወዲ አረቢያው ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኩባንያጋር በትብብር የጥገና ስራ ለማከናወን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በዚህ ስምምነት ሁለቱ ተቋማት ረዥም ጊዜ የሚቆይ የአውሮፕላን ጥገና አገልግሎት በትብብር መስራት የሚያስችላቸው ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የሳወዲ አየር መንገድ በአፍሪካ እና በሳወዲ በሚኖራቸው በረራዎች ለደንበኞቻቸው አገልግሎት ጥራት በጋራ መስራት ያስችላቸዋልም ተብሏል።

ይህን ስምምነት የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቴክኒክ ክፍል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም ፀሃይ እና የሳዑዲው ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ዋና ዳይሬክተር አሊ አል አሽባን ናቸው።

et_saudi.jpg

አቶ ዘላለም፥ “በመካከለኛው ምስራቅ እና በባህር ሰላጤው ለምንሰጠው የበረራ አገልግሎት የመግባቢያ ስምምነቱ ትልቅ ፋይዳ አለው ማለታቸውን” የሳውዲ ጋዜጣ በድረ ገፁ አስፍሯል።
የሳውዲው አቻቸው አሊ አል አሽባን በበኩላቸው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቴክኔክ ክፍል ጋር ያደረጉት ስምምነ የሁለቱን ኩባንያዎች የረዥም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።