በመዲናዋ የሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ህብረት ስራ ማህበራት ካፒታል ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ህብረት ስራ ማህበራት ካፒታል ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል።

የማህበራቱን የቁጠባ ካፒታል በ2010 ዓ.ም ወደ 5 ቢሊየን ብር ለማድረስ ታቅዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ቀንን ዛሬ አክብሯል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረ ኪዳን ገብሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፥ ነባር እና አዳዲስ ህብረት ስራ ማህበራት በገንዘብ ቁጠባ የሚደራጁበት እና ተጠቃሚ የሚሆኑበት አዲስ የመዋቅር ለውጥ እና አደረጃጀትም እየተተገበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከ180 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፉ 1 ሺህ 102 መሰረታዊ እና ሁለት ዩኒየን የቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት አሉ።

በቤቴልሄም ጥጋቡ