ከውጭ ምንዛሪ ማሻሻያው በፊት በገቡ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ ማሻሻያ ከመደረጉ በፊት ወደ ሀገር ውስጥ በገቡ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ከማሻሻያው ቀደም ብለው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ምርቶችና የሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ጭማሪ አይደረግም ብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ተመኑን መሻሻል ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ ሸቀጦችን የሚደብቁ እና የሚያከማቹ ነጋዴዎች እንዳሉ ጥቆማ ደርሶኛልም ነው ያለው ባለስልጣኑ።

ይህን ተከትሎም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ገበያውን ለማረጋጋትና ህገወጦችን ለህግ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል።