በጥቅምት ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጥቅምት ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ዋጋ በመስከረም ወር በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የአውሮፕላን ነዳጅ በመስከረም ወር ሲሸጥበት ከነበረበት 15 ብር ከ80 ሳንቲም የ72 ሳንቲም ጭማሬን ያሳያል ተብሏል።

በዚህም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በ16 ብር ከ52 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውጪ ያለ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በመስከረም ወር በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድ ሚኒስቴር ገልጿል።