የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መለያ አርማውን ቀየረ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ የመለያ አርማውን ቀየረ።

ተቋሙ በ2009 የስራ አፈጻጸም ደረጃዎችን በአዲስ መልክ ማዘጋጀት እና መከለስ በኩል ጥሩ ስራዎች ቢሰሩም ደረጃዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ክፍተቶች እንዳሉ አሳውቋል።

ደረጃዎችን ለማስተገበርም በፊት የሚታወቀውን አስገዳጅ የምርት ምልክቱ አለመቀየሩን ነው ያመለከተው።

የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይስማ ጅሩ እንዳሉት በሀገሪቱ ለምርትም ሆነ ለአገልግሎት ትልቁ ገዥ መንግስት በመሆኑ በግዥ ስርአቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ደረጃዎች እንደ አንድ መስፈርት ጥቅም ላይ እንዲውል እና ደረጃዎች እንዲተገበሩ ጥረት እየተደረገ ነው።

በዚህም ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመሆን ከ600 በላይ ደረጃዎች በግዥ ስርአት ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ምርቶችን ሲገዛ የኤጀንሲው አስገዳጅ የምርት ምልክት ያለበት መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸውም ነው ያሉት።

 

 

በቤተልሄም ጥጋቡ