የደረጃ “ሐ” የግብር ከፋዮች የግብር መክፈያ ቀን ለተጨማሪ 10 ቀናት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ያሉ የደረጃ “ሐ” የግብር ከፋዮች ግብር የመክፈያ ቀን ለተጨማሪ 10 ቀናት ተራዘመ።

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን የአዲስ አደበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፥ ቀኑን ማራዝም ያስፈለገው ከቀን ገቢ ግምታው ቅሬታ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በቆየው ጫና ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ የተነሳም ግብር ከፋዮችን በተፈለገው መልኩ ማስተናገድ አልተቻለም ያለው ጽህፈት ቤቱ፥ በዚህ ምክንያት ቀኑን ማራዘም እንዳስፈለገም ገልጿል።

ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች እስካሁን 80 በመቶዎቹ ዓመታዊ ግብራቸውን መክፈላቸውን ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ግብር መክፈያ ቀኑ ለቀሪዎቹ 20 በመቶዎቹ ሲባል እስከ ነሐሴ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ መራዘሙም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን የአዲስ አደበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እስታውቋል።

ግብር ከፋዮች አላስፈላጊ ለሆነ ቅጣት ላለመዳረግም ዛሬን ጨምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጥሪ ተላልፏል።