በኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ መድረክ በህንድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ መድረክ ነገ በህንድ ይካሄዳል።

የህንዱ ፋይበር ቱ ፋሽን የተባለው ድረ ገጽ እንዳስነበበው፥ መድረኩ ህንዳውያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን እንዲረዱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡

በመድረኩ ላይ በተለይም በኢትዮጵያ ለውጭ ባለሃብቶች ያሉ ማበረታቻዎችን በተመለከተ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል።

መድረኩ በዘርፉ የተሰማሩ የህንድ ባለሀብቶችና የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የልምድ ልውውጥ የሚያካሂዱበትና ዘርፉን ለማሳደግ የሁለትዮሽ ስምምነት የሚፈጥሩበት ይሆናል ተብሏል።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማሳደግ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን የተቀሰው ድረ ገጹ፥ ሀገሪቱን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማዕከል ሊያደርጉ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እየተገነቡ መሆናቸውን ገልጿል።

ሀገሪቱ በአስር ዓመታት የዓለም የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ማዕከል ትሆናለች ያለው ዘገባው፥ በሃገሪቱ ያለው ከ47 ሚሊየን በላይ የሰራተኛ ሃይል ለዘርፉ ምቹ አጋጣሚ መሆኑን አንስቷል።

አሁን ላይ በሃገሪቱ ለው የሃይል አቅርቦት ለዘርፉ ምቹ አጋጣሚ መሆኑንም ነው ዘገባው የጠቀሰው ዘገባው፤ አንድ ኪሎዋት ኤሌክትሪክ በ0 ነጥብ 04 ዶላር መሸጡን በማሳያነት በማንሳት።

ከዚህ ባለፈም በማምረቻው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከውጭ የሚያስገቧቸውን እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ የሚደረገው ማበረታቻ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላሉ መልካም አጋሚዎች ማሳያ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

 

 


ምንጭ፦ fibre2fashion.com