ከ2 ሚሊዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ2 ሚሊዬን 116ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች፣ ኮስሞቲክስ፣ የተለያዩ አልባሳት፣  ጫት፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ መድሃኒት የተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው።

ዕቃዎቹ የተያዙት በብየቆቤ እና በሀረር የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ከሰኔ 26 እስከ ሃምሌ አንድ ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ነው።

የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ትምህርት እና ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ወይዘሮ ዘቢደር በርሲሳ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገው

በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ አባላት፣ በክልሉ የጸጥታ አካላትና የአካባቢዉ ህብረተሰብ ባደረጉት ትብብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ወይዘሮ ዘቢደር በአዲሱ ገቢ ግብር እና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ዙሪያ በሐረር ከተማ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች ስልጠና መሰጠቱንም ጠቁመዋል፡፡

 

 


ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን