የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዲስ የቡና ግብይት ስርአት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 5፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አዲስ የቡና ግብይት ስርአት ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በዛሬው እለት አዲሱ የግብይት ስርዓት ስራ መጀመርን ይፋ አድርጓል።

የምርት ገበያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ፥ ዛሬ ይፋ የተደረገው የቡና ግብይት ስርዓት በዘርፉ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ማሻሻያዎች የተደረጉበት ነው ብለዋል።

ስርአቱንም ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እንደተደረገበት አቶ ኤርሚያስ ገልጸዋል።

የቡና ቅበላ ለሚካሄድባቸው መጋዘኖች ሰራተኞች ስለ አዲሱ የግብይት ስርአት ስልጠና መሰጠቱን ስራ አስፈጻሚው አብራርተዋል።

ምርት ገበያው ለቡና ግብይቱ የምርት ባለቤትነትንና መገኛን ገላጭ የሆነ የመኪና ላይ አዲስ የግብይት ስርዓት አዘጋጅቶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

የግብይት ስርዓቱም የምርቱንና የምርቱን ባለቤት ማንነት ባስጠበቀ መልኩ የሚካሄድ ሲሆን፥ ምርቱ ወደ መጋዘን ሳይገባ በተከለለ ጥብቅ ማቆያ (ቦንድድ ያርድ) ውስጥ በመኪና ላይ እንዳለ መሸጥ የሚያስችል ነው።

የግብይት ስርአቱ የምርት ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ ባሻገር አርሶ አደሮች የግብይት መስፈርቱን ካሟሉ በቀጥታ መገበያየት እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።

 


በምስክር ስናፍቅ