ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የሲሚንቶ ፣ኮንክሪት እና ኃይል ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲስ አበባ ሚያዚያ 9/2009 በምስራቅ አፍሪካ የሲሚንቶ ፣ኮንክሪት እና ኃይል አቅም ማሳደግ አስመልክቶ የሚወያያ ጉባኤ በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት የጉባዔ አደራሽ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል፡፡

አመታዊ ጉባኤው ከሚዚያ 11 -12 /2009 ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥የሶስቱ ዘርፎች ኢንዱስትሪዎች በቀጠናው በትብብር ፣ በእውቀት ሽግግር እና በስትራቴጂክ አጋርነት በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ የሲሚንቶ ፣ኮንክሪት እና ኃይል ጉባኤ በቀጠናው ሀገራት ውስጥ የሲሚንቶ፣ የኮንክሪት እና የሃይል ኢንዱስትሪዎች እንዲያድጉ እና ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው፡፡

ባለፈው አመት በተካሄደው ጉባኤ የስድስት ሀገራት ተወካዮች በሲሚንቶ ፣ኮንክሪት እና የሃይል ኢንዱስትሪዎች መካከል ስትራቴጂክ ትብብር ምፍጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ተወያይተው ነበር፡፡

ሁለተኛው ጉባኤ በአዳማ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሲሚንቶ ቴክኖሎጂ ማዕከል ከስትራቴጂክ ተባባሪዎቹ የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብኣቶች ልማት ኢንስቲትዩት ፣የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ማህበር ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡፡፡

ምንጭ፦www.icanetpitalafrica.