የየካቲት ወር የዋጋ ግሽበት በ0 ነጥብ 9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 7 ነጥብ 0 ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ግሽበቱ ባለፈው ወር ከነበረበት 6 ነጥብ 1 በመቶ በዚህ ወር ወደ 7 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

በዚህም ግሽበቱ ባለፈው ወር ከነበረበት የ0 ነጥበ 9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በወሩ ምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት 7 ነጥብ 8 በመቶ ሆኖ ሲመዘገብ ካለፈው ወር የ2 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ንጻሩ ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የ6 ነጥብ 2 በመቶ ግሽበት ሲመዘገብ ካለፈው ወር የ1 ነጥብ 2 በመቶ ቅናሽ ተመዝግቦበታል፡፡