5ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ ፣ ጥር 2 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ 5ኛውን የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ልታስተናግድ ነው፡፡

ከፎረሙ ሶስት ቀን ቀደም ብሎ በዱባይ የፎረሙ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ይካሄዳል፡፡

በውይይቱ ላይ በአሁጉረ አፍሪካ ኢንቭስት ሊያደርጉ የሚችሉ ባለሃብቶች ይታደማሉ፡፡

ውይይቱ በፋይናንስ እና ካፒታል ኢንቨስትመንት፣ በአይ ሲ ቲ፣ ግብርና፣ በማዕድን እንዲሁም በሃይል አቅርቦት ዘርፍ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

ከዚህ ባለፈም መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች፣ አቪየሽን ዘርፍ፣ መሰረተ ልማት፣ ቱሪዝም፣ የማምረቻ ዘርፍ እና ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች የውይይቱ አጀንዳዎች ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም የአህጉሩኑ ባለሃብቶች ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሌሎች ሃገራት ባለሃብቶች ጋር በማገናኘት ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡

በፎረሙ ከፍተኛ መንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ አምባሳደሮች፣ ባለሃብቶች እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ይገኛሉ፡፡

የፊታችን የካቲት መጨረሻ ላይ በሸራተን አዲስ የሚካሄደው የቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ ሲዘጋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

 


ምንጭ፦ አፍሪካ ቢዝነስ ፎረም