በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባደረሰን መግለጫ ባለፉት ሶሰት ወራት በዓለም ገበያ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በተከታታይ ጭማሪ ማሳየቱን ገልጿል።

ይህንን ጭማሪ መነሻ በማድረግም አሁን ስራ ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ መከለስ አስፈልጓል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።

በዚህም መሰረት ቤንዚን በሊትር 16 ብር ከ61 ሳንቲም የነበረው በተከለሰው ዋጋ 17 ብር ከ92 ሳንቲም ሆኗል።

ነጭ ናፍጣ 14 ብር ከ16 ሳንቲም የነበረው 15 ብር ከ18 ሳንቲም እንዲሆን ተደርጓል።

ጭማሪ በተደረገበት ዋጋ መሰረት ኬሮሲን በሊትር 13 ብር ከ65 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 13 ብር ከ57 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 12 ብር ከ93 ሳንቲም ሆኗል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ በሊትር 15 ብር ከ49 ሳንቲም መሆኑን ሚኒስቴሩ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህ የዋጋ ማስተካከያም ከነገ ጥር 2 እስከ ጥር 30 2009 ዓመተ ምህረት ድረስ ተግባራዊ ይደረጋል ነው ያለው ንግድ ሚኒስቴር።

android_ads__.jpg