የበዓል ማድመቂያዎችን በተሻለ አማራጭና ተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ መሆኑን የመዲናዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የገና ዋዜማ ቀናትን በደራ ገበያ ሞቅ ባለ ድባብ እያስተናገደች ነው።

በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል እና ሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄዱ ባዛሮች ሞቅ ደመቅ ያለ የበዓል ግብይት እየተካሄደ ነው፡፡

በዓሉን አስታኮ በተዘጋጀው ኤግዚቪሽን ላይ የቀረቡ ምርቶችም በብዛት እየተገበዩ ሲሆን፥ የከተማዋ ነዋሪዎችም በቦታው ያለው ግብይት ጥሩ የሚባል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሸማቾች የሚያስፈልጋቸውን የበዓል ማድመቂያ የሆኑ የስጦታ እቃዎች፣ የባልትና ውጤቶችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን በተሻለ አማራጭ ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር እያገኙ መሆኑንም ነው የሚናገሩት፡፡

ነጋዴዎች በበኩላቸው ባዛሮቹ ከምርት ሽያጭ ባሻገር ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እንደረዳቸው ያነሳሉ።

የቁም እንስሳት ግብይት በሚካሄድባቸው ሾላ ገበያ እና ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው በግ ተራም የቁም እንስሳትን ለሽያጭ ባቀረቡ ነጋድዎች እና ተገበያዮች ተሞልቶ ውሏል።

በእነዚህ የግብይት ማዕከላት የበግ እና ዶሮ ሽያጭ ከሌሎቹ የእርድ እንስሳት በበለጠ መልኩ ግብይት እተካሄደበት ይገኛል፡፡

በሾላ ገበያ በግ ከ750 ብር ዶሮ ደግሞ ከመቶ ሃያ ብር ጀምሮ ይጠራል።

አጠቃላይ በግብይት ማዕከላቱ ጥሩ የእርድ እንስሳት አቅርቦት ስለመኖሩም ተገበያዮች ይገልጻሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም በከተማዋ በአንዳንድ የህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ባደረግነው ቅኝትም፥ ጥሩ የስኳር እና ዱቄት አቅርቦት መኖሩን ታዝበናል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ እና በልደታ ክፍለ ከተማ አንዳንድ የሸማች ማህበራት ሱቆች ግን የዘይት አቅርቦት መዘግየት ተስተውሏል፡፡

በይሄነው ዋጋቸው

android_ads__.jpg