ቢዝነስ

አዲስ አበባመስከረም 30፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ፤ ኢሉ አባቦራ ዞን፤ ያዩ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው 20 በመቶ መድረሱን የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የመስከረም ወር አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት በአማካይ 5 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያና ፊሊፒንስ የበረራ መዳረሻቸውን በጋራ ማሳደግ የሚያስችላቸውን የበረራ ስምምነት አደረጉ።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በተያዘው የበጀት ዓመት በማምረት ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎች ከ49 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምርት እንዲያመርቱ በትኩረት እንደሚሰራ የብረታ ብረትና ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የንግድ ሚኒስቴር በመስከረም ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥቅምት ወርም ባለበት እንዲቀጥል ወሰነ።