በደቡብ ካስትል ዋንጫ ሲዳማ ቡና ድል ሲቀናው አርባ ምንጭና ድሬ ዳዋ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትናንትናው እለት የተጀመረው የደቡብ ክልል የካስል ዋንጫ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በሀዋሳ ስታዲየም ተካሂዷል።

በዛሬው እለትም ምድብ ለ ውስጥ የተደረሉት ክለቦች ጨዋታቸውን አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ዛሬ 8 ሰዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ ከድሬ ደዋ ከተማ ተገናኝተው ጨዋታቸውን ያካሄዱ ሲሆን፥ ጨዋታውም ያለ ምንም ግብ 0ለ0 በሆነ የአቻ ውጤት ተጠናቋል።

10 ሰዓት ላይ የተካሄደው ጨዋታ ደግሞ ሲዳማ ቡናን ከተጋባዡ ወልዲያ ከተማ ጋር አገናኝቷል።

ጨዋታውንም ሲዳማ ቡና 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታው ላይ ባዬ ገዛኸኝ በ14ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሀብታሙ ገዛኸኝ በ22ኛ ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።

በትናንትናው እለት በተካሄደው የምድብ ሀ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን ረቷል።

በምድብ "ሀ" የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ባደረጉት ጨዋታ ፋሲል ከነማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለፋሲል ከነማ ፊሊፕ ዳውዝ ሁለት ኤርሚያስ ሀይሉ አንድ የማሸነፊያ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።

ለሀዋሳ ከተማ በባዶ ከመሸነፍ ያዳነችውን ግብ ፍሬው ሰለሞን በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

በሌላ የምድቡ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 ረቷል።