በባግዳድ በአንድ የገበያ ስፍራ በደረሱ ፍንዳታዎች 28 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢራቅ መዲና ባግዳድ በአንድ የገባያ ስፍራ በደረሱ ሁለት የቦምብ ፍንዳታዎች 28 ሰዎች ሞቱ።

በከተማዋ በሚገኝ የመኪና መለዋወጫ አቅራቢያ በአልሲናክ የገበያ ስፍራ ውስጥ በአንድ አጥፍቶ ጠፊ እና በተጠመዱ ሁለት ቦምቦች ነው ጥቃቶቹ የደረሰው።

በፍንዳታዎቹ 28 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል።

ለጥቃቱ ጽንፈኛው ታጣቂ ቡድን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ገልጿል።

ቡድኑ ከጥቃቱ በኋላ በሰጠው መግለጫ ሁለት ታጣቂዎቹ በአጥፍቶ መጥፋት ተልዕኮ ጥቃቱን ፈጽመዋል ብሏል።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ