በቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦችና የልብ ጤና

አዲስ አበባ፣ሃምሌ፣4፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ጤናን ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋዕኦ እንዳላቸውና ከበርካታ በሽታዎች ለመከላከል እንደሚያስችሉ ይነገራል።

ሆኖም ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት አዲስ ጥናት በቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦች ለልብ ጤና ጥቅም እንደሌላቸው ተገልጿል።

በጥናቱ በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦችና በልብ ጤና ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖና ጥቅም የሌለው መሆኑ ተመልከቷል።

ይህ ጥናት በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦች ከልብ፣ ስትሮክ እና ካርዲዮቫስኩላር በሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሞትን ለመከላከል ያስችላል የሚለውን የባለሙያዎች ክርክር ፍፃሜ እንዲያገኝ ይረዳል ተብሏል።

ተመራማዎቹ በባለሙያዎች ትዕዛዝ በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦች ካርዲዮቫስኩላር እና ለሌሎች በሽታዎችን ሰዎች ለመከላከል እንዳይጠቀሙት የሚደረገውን ጥረት ድጋፍ ለማድረግ ያስችሏል።

ተመራማሪዎቹ በቫይታሚንና በማዕድናት ከበለፀጉ ምግቦች በተሻለ ለልብ ጤና ወሳኝ የሆነ አመጋገብ፣ የአካል እንቅስቃሴ፣ የደም ግፊትንና ጤናማ ያልሆነ

የኮሌስትሮል መጠንን መቆጣጠር እና የህክምና ክትትል ማድረግ የተጠቀሱትን በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል ተብሏል።

በአሜሪካ ከፈረንጆቹ 1940 ጀምሮ በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦችን የሚያመርቱ በርካታ ሚሊየን ዶላሮቹን የሚያንቀሳቅሱ ኢንዱስትሪዎች እንደተቋቋሙ ይነገራል።

በዚህ ምክንያት ከአሜሪካ ዜጎች አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦችን እንደሚጠቀሙ ተነግሯል። 

ይህም በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦች ካርዲዮቫስኩላር እና ሌሎች በሽታ ለመከላከል ያስችላል የሚል አመለካከት በበርካቶች ዘንድ እንዲፈጠር ተደርጓል።

ከ2 ሚሊየን በላይ ሰዎች የተሳተፉበት ይህ ጥናት 12 ዓመታትን የፈጀ መሆኑ ተነግሯል። 

በዚህም በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦች መጠቀምና ከካርዲዮቫስኩላር ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሞት ግንኙነት እንደሌላቸው ማረጋገጣቸውን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።

ተመራማሪዎቹ በቫይታሚንና በማዕድናት የበለፀጉ ምግቦች መጠቀምና የካርዲዮቫስኩላር በሽታዎች ውጤቶችን በተመለከተ ጥናት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ምንጭ፡- medicalnewstoday