የተፈጥሮ ስብ የህምም ስሜት እንዳይሰማ ያደርጋሉ- ጥናት

አዲስ አባባ፣ ሃምሌ 02 ፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተፈጥሮ ስብ የህምም ስሜት እንዳይሰማ በማድረግ በሽታን ሊያባብሱ እንደሚችል አንድ ጥናት አመላክቷል።

የተፈጥሮ የሰውነት ስቦች የህመም ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ ለከፋ በሽታ ሊያጋልጡ አንደሚችሉ ተመላክቷል።

በተፈጥሮ በሰውነታቸን ውስጥ የምናገኛቸው የስብ ክምችቶች ሰውነታችን ለባክቴሪያ ወይንም ቫይረስ ሲጋለጥ ቶሎ የህመም ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ ለከፋ በሽታ ሊጋልጡን እንደሚችል ተገልጿል።

በጥናቱ እንደተገለጸው ሰውነታችን ለበሽታ የሚያጋልጡ ባክቴሪያዎች ወይንም ቫይረስ ወደ ሰውነታችን እንደገቡ የተፈጥሮ ስቦች የህመም ስሜት ሳይሰማን እንዲቆይ በማድረግ የህመም ደረጃው ከፍተኛ ሁኔታ ላይ ሳይደረስ ክትትል እንዳናደርግ የሚያዘናጉ መሆኑ ተመላክቷል።

ተመራመሪዎቹ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ስቦች ላይ ባደረጉት የቤተ ሙከራ ምርምር ተመሳሳይ ውጤቶችን ማግኝታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ሰውነታችን ለበሽታ የሚያጋልጡ ተህዋሲያን ሲጋለጥ ወዲያውኑ የህመም ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ነው ጥናቱ ያመላከተው።

ተመራማሪዎች በአይጦችና ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት እንዳረጋገጡት የሰወነት ውስጥ የተፈጥሮ ስብ ክምችት ሰውነት ለባክቴሪያም ይሁን ለቫይረስ ሲጋለጥ ቶሎ የህመም ስሜት እንዳይሰማን በማድረግ በሽታ እንዲባባስ የሚያደረጉ መሆኑ ነው የተገለጸው።

 

 

ምንጭ፦ upi.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ