የአየር ንብረት ብክለት ለስኳር ህመም ያጋልጣል - ጥናት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለማችን ከ420 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ እንዲሁም እጅግ በመስፋፋት ላይም እንደሚገኝም መረጃዎች ያመለክታል፡፡

ቀደም ብለው ይፋ የሆኑ ጥናቶች ከስኳር ህመም ምክንያቶች መካከል ስርዓቱን ያልጠበቀ የአመጋገብ ስርዓት፣ ውፍረት እና ሌሎችም ሲሆኑ አዲሱ ጥናት ግን ከነዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረት ብክለትም አስተዋፅዖ ያደርጋል ብሏል፡፡

አዲሱ ጥናት በአየር ንብረት ምክንያት በ2016 ብቻ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎችን በህመሙ እንዲያዙ ማድረጉን ያሳየ ሲሆን፥ ይህም ማለት 14 በመቶውን ይይዛል፡፡

እንዲሁም ከአየር ንብረት ጋር ግንኙነት ባለው የስኳር ህመም ምክንያት 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ገምቷል፡፡

በአሜሪካ ውስጥ ብቻ 30 ሚሊየን በስኳር ህመም የተያዙ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን፥ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በየዓመቱ 150 ሺህ አዳዲስ ተጠቂዎች እንደሚቀላቀሉ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በጥቅሉ ከአየርንብረት ጋር በተያያዘ የ350 ሺህ ሰዎች ህይወት እንደሚያልፍም ጥናቱ አሳቷል፡፡

ጥናቱ ከአየር ንብረት ጋር በተገናኛ በስኳር ህመም በከፍተኛ ሁኔታ ይጋለጣሉ ካላቸው ሀገራት መካከል አፍጋኒስታን፣ ፓፓዋ ኒው ጊኒ እና ጉያና መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የመጋለጥ ዕድላቸውዝቅተኛ ከሆኑ ሀገራት መካከል ደግሞ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ እና አይስላንድ ተጠቅሰዋል፤ አሜሪካ አማካይ ቦታ ላይ ተቀምጣለች ተብሏል፡፡

 

 

 


ምንጭ፦ሳይንስ ዴይሊይ
በአብርሃም ፈቀደ