የአካል ብቃትና አዕምሮ እንቅስቃሴ የመማር አቅምን ያሳድጋል- ጥናት

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዚህ በፊት የአካል ብቃትና አዕምሮ እንቅስቀሴ ለአዕምሮ ጤና ወሳኝ እንደሆነ ይነገረ ነበር አዲስ የወጣ ጥናት ደግሞ የመማር አቅምንም እንደሚያሳድግ ጠቁሟል።

ከዚህ በፊት እንቅስቀሴ ማድረግ መርሳትን እና ሌሎች አዕምሮ ጤና ችግሮችን ለመከላከል እንደሚረዳ በጥናት ተረጋግጧል።

ይህ ጥናት ደግሞ በልጅነትና ወጣትነት የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች አካል እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ከአዕምሮ ጤና በተጨማሪ በትምህርት ህይወታቸው ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ይህ ጥናት የነርቭ ህዋሳት ግንኙነት እና ለትምህርት አቅም ወሳኝ የሆኑ አካል ክፍሎችን በመለካት ውጤታማ መሆን እንደተቻለ ተነግሯል።

ይሄ ውጤት ለአዕምሮ የትምህርት እድገት ወሳኘ በሆነው ሂፖካምፓስ የአዕምሮ ክፍል ተገኘቷል።

እንዲሁም ጥናቱ ልጆችን እንዴት ማሳደግ እንዳለብንና በልጅነታቸው የሚያዙበት መንገድ የትምህርት አቅማቸውን ሊወስን እንደሚችል አሳይቷል ተብሏል።

ሆኖም ይህ ውጤት በአሁኑ ሰዓት በአይጦች ላይ በተደረገ ሙከራ ላይ የተገኘ በመሆኑ በሂደት በሰው ላይ ውጤታማነቱን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተገልፃል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በኤፍሬም ምትኩ