ለጉሮሮ ጤንነት የሚመከሩ ተግባራት

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎሮሯችን ውስበስብነት ባላቸው ቲሹዎች፣ ነርቮች፣ እጢዎች እንዲሁም የደም ቧንቧዎች የተሞላ የሰውነታችን አካል ክፍል በመሆኑ የተለየ ጥንቃቄ ይሻል።

ስለዚህም ለጉሮሯችን ጤንነት አስፈላጊ የሚባሉ የጥንቃቄ መንገዶችን እንጠቁምዎ።

1 ጎሮሯችንን ካልተስካከለ የሙቀት ወይም የቅዝቃዜ መጠን መጠበቅ

ከሰውነታችን ብዙ የሙቀት መጠን በአንገታችን ይወጣል ይህንንም ለመከላከል ስካርቭ ወይም የአንገት ሹራብ የመልበስ ልማዳችንን ብናዳብር ለአንገታችን ጤንነት የሚመከር ነው።

2 የመመገቢያ ቁሳቁሶችን ከሌሎች ጋር አለመጋራት

ከሌሎች ጋር የመመገቢያም ሆነ የመጠጫ ቁሳቁሶችን ፈፅሞ አለመጋራት ምክንያቱም በቀላል ንክኪ ለሚመጡ የጎሮሮ ህመሞች ሊያጋልጠን ይችላል እና።

3 የጥርስ ቡሩሻችንን በደንብ ማፅዳት

ብዙዎቻችን ልብ የማንለው ችግር ሲሆን የጥርስ ቡርሻችንን ውጪ በሚቆይበት ጊዜ ብዙ ባክቴሪያዎች ሊይዝ ይችላል።

በዚህም ጥርሳችን በምንፀዳበት ጊዜ ለተለያዩ በሽታዎች መፈጠር እንደ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ስለዚህም የጥርስ ቡርሻችንን ከመጠቀማችን በፊት ጨውና ሙቅ ውሀ ድብልቅ ውስጥ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አቆይተን መጠቀም ይኖርብናል።

4 በጨው መጉመጥመጥ

ይህ ዘዴ ጊዜ የማይሽረው እና ለረጅም ጊዜያት የሚታወቅ እንደሆነ ይነገራል።

ማታ ላይ ለብ ባለ ውሀ እና ትንሽ ጨውን በማደባለቅ ጉሮሮ ላይ ይዞ መጉመጥመጥ ለጉሮሮ ሁነኛ መድሀኒት እንደሆነ ይነገራል።

በተለይም ጉንፋን፣የጉሮሮ ኢንፌክሽን እና በመሳሰሉት በምንያዝበት ጊዜያት ይህን መንገድ መጠቀም ፍቱን እንደሆነ ይመከራል።

5 የማር እና የዝንጅብል ድብልቅ

ጠዋት ጥርስዎን ከቦረሹ በኋላ ከሶስት እስከ አራት ሚሊ ግራም የሚሆን ዝንጅብል በመጭመቅ ከ አምስት ሚሊ ግራም ማር ጋር ደባልቆ መጠቀም ቀኑን ሙሉ ጥሩ ስሜት እየተሰማዎት ይውላሉ።

6 የድምፅ ሟሟቂያዎችን ጠዋት ላይ መለማመድ

ዘፋኞች፣አክተሮች፣ዶክተሮች፣ጋዜጠኞች የመሳሰሉ ሙያዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ይህን ልምምድ በየቀኑ ማዳበር እንደሚጠበቅባቸው ይነገራል።

የዚህም ምክንያት ከሌላው ማህበረሰቦች እነኚህ ሙያዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች ጉሮሮዋቸውን አብዝተው ስለሚጠቀሙ እንደሆነ ይነገራል።

ምንጭ፦ሄልዝ ዳይጀስት