ስለ ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የካንሰር ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ የካቲት 4 ይከበራል።

አላማውም በዓለማቀፍ ደረጃ ላይ መንግስትን እና ግለሰቦች ስለ ካንሰር ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በየዓመቱ በሚሊየን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል ሞትን መከላከል ነው።

በዚህም ሲ ጂ ቲ ኤን “ስለ ካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ?” በሚል ርእስ መረጃ አዘል ፅሁፍ ይዞ ወጥቷል።

1. በጣም ገዳይ ካንሰር የሚባለው የትኛው ነው?

የሳንባ ካንሰር በዓለም ላይ ካሉት የካንሰር አይነቶች ቅድሚያ የሚጠቀስ ሲሆን፥ ይህም ለሞት የሚዳርግ ገዳይ የካንሰር ዓይነት ነው።

የአለም ጤና ድርጅት በጣም የተለመዱ እና ገዳይ የካንሰር በሽታዎች ብሎ በዝርዝር የጠቀሳቸውም፥ የሳንባ፣ ጉበት፣ አንጀት፣ ሆድ እና ጡት ካንሰሮች ናቸው።

2. ካንሰር ሊዛመት ይችላልን?

2.png

ካንሰር ተላላፊ ህመም ስላልሆነ፥ ጤናማ የሆነ ሰው ካንሰር ካለው ሰው ህመሙ ሊይዘው አይችልም።

እንደ አሜሪካ የካንሰር ማህበር ካንሰር በመቀራረብ ወይም እንደ ወሲብ፣ መሳሳም፣ መነካካት፣ ምግብን በጋራ በመመገብ ወይም በትንፋሽ ከአንዱ ሰው ወደ ሌላው ሰው ሊዛመት እንደሚችል የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም።

3. ለሳንባ ካንሰር መነሻ የሚሆነው ምንድን ነው?

3.png

የሳንባ ካንሰር ሲጋራ በማጨስ፣ አጫሾች ባሉበት ቦታ ለሚኖረው የሲጋራ ጭስ መጋላጥ፣ በአየር ብክለት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።

በተጨማሪም በሥራ ቦታ ከፋብሪካዎች ለሚወጣ ብናኝ መጋለጥ እና አንዳንድ ኬሚካሎች የሳንባ ካንሰርን ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሏል።

4. "ሮዝ ሪባን" በአለም አቀፍ ደረጃ ለምን ዓይነት ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ የሚረዳ ምልክት ነው?

4.png

ሮዝ ሪባን (Pink Ribbon) በዓለም አቀፍ ደረጃ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ለማሳደር የሚረዳ ምልክት ነው።

በዚህም ሮዝ ሪባን እና ቀለሞቹ በአጠቃላይ የተሸከመው መልእከት፥ “የጡት ካንሰር ላለባቸው ሴቶች የሞራል ድጋፍ እንስጥ” የሚል ነው።

5. ካንሰር በዘር የሚተላለፍ በሽታ ነውን?

5.png

መልሱ አዎ ካላችሁ ትክክል ነው፤ ምክንያቱም ካንሰር በጣም ከተለመዱ የሰው ዘረመል በሽታዎች አንዱ ስለሆነ።

ዘገባው እንደሚያሳየው በአንዳንድ ሁኔታዎች በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ የካንሰር በሽታዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ በሚተላለፍ ያልተለመደ ጂን ሊከሰቱ ይችላሉ።

ይህም የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው ከ5 እስከ 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ከወላጅ በተወረሱት ሙታሽንስ (mutations) በሚባል የጂን ጉድለት በቀጥታ እንደሚከሰቱ ይታመናል።

6. ካንሰር ሊታከም ይችላል?

6.png

ካንሰር ከ100 ለሚበልጡ በሽታዎች አጠቃላይ ስም ሲሆን፥ አንዳንዶቹ የካንሰር በሽታ አይነቶች ሊድኑ እንደሚችሉ ነው የተገለፀው።

በአሜሪካ የካንሰር ማህበር እንደገለፀው፥ የጡት ካንሰር፣ አብዛኛዎቹ የቆዳ ካንሰሮች፣ የቆለጥ ካንሰር እና እድገትን የሚቆጣጠር እጢ (ታይሮይድ)ካንሰር በከፍተኛ ህክምና ሊፈወሱ ከሚችሉ ካንሰሮች ጥቂቶቹ ናቸው።

በተጨማሪም ማህበሩ እንደሚጠቁመው ከሆነ፥ በብዙ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ እየተደረገ ባለ ምርምር ብዙ የካንሰር አይነቶች ለመፈወስ የሚያስችል ዕድልን እየጨመረ ነው።

7. ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

7.png

የዓለም የጤና ድርጅት ከ30 እስከ 50 በመቶ የሚደርሱ የካንሰር ዓይነቶች ለበሽታው ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ራስን በመጠበቅ እና የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመጠቀም ልንከላከላቸው የምንችላቸው ናቸው።