የአዕምሮ ጤንነትን ለማሻሻል የሚረዱ የእለት ተዕለት ተግባራት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ከአዕምሯዊ ጤንነታቸው ጋር ከመታገል ይልቅ፥ በዕለት ተዕለት የሚያዳብሯቸው ትናንሽ ደረጃዎች እና ልምዶች የአዕምሮ ጤንነት እና ደስተኛነት ለማረጋገጥ ያግዛሉ።

በዕለት ተዕለት የህይወት ልምዶች ውስጥ በቀላሉ በማካተት የአዕምሮ ጤንነት ለማሻሻል የሚረዱ መንገዶች አሉ።

1. በልበ ሙሉነት መራመድ

አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው ጭንቅላት ቀና በማድረግ ትክሻዎን ነፍቶ መራመድ ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎት ሊያደርግ ይችላል።

happy_2.jpg

2. ሁሉንም ነገሮች በማተኮር ስዕል ከማንሳት መቆጠብ

ፎቶግራፍ ብዙ ነገሮች ለማስታዎስ ሊረዳ እንደሚችል ይታወቃል፤ ነገር ግን በስነልቦና ሳይንስ የታተመ አንድ ጥናት ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይላል።

የማስታወሻ ፎቶግራፍ በምናነሳበት ጊዜ ሁሉንም ነገር (የሚያስፈልገን እና የማያስፈልገን) ከማንሳት ይልቅ በምንፈልገው ነገር ብቻ ማተኮር ለአዕምሮ ጤንነት ጠቃሚ እንደሆነ በስነ ልቦና ባለሙያዎች የተደረገው ጥናት ያመላክታል።

3. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

በለንደን ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ጥናት እንደሚያሳየው፥ በሳምንት ሶስት ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የመጨናነቅ ስሜት በ19 በመቶ ይቀንሳል።

ተመራማሪዎቹ እንደሚያሳዩት ንቁ ሰዎች በጭንቀት የመያዝ ዕድላቸው ዝቅተኛ ሲሆን፥ የተጨነቁ ሰዎች ደግሞ ንቁ መሆን አይችሉም።

Exercise.jpg

4. በፕሮግራም ላይ ለዛሬ ለነገ ማለትን ማቆም

ሥራዎን ለመስራት የሚያስቀምጡት ረዥም ጊዜ ስራ ለመስራት ካለዎት ፍራቻ ወይም ጭንቀት እንደሚመነጭ ያመላክታል፤ በዚህም የአዕምሮ ነርቭ ይበልጥ ለማስጨነቅ እና ለማዳከም የሚያስችል ሁኔታ ሊከሰት ይችላል።

ስለዚህ የፈለጉትን ስራ ለማስራት ሙዚቃን በማዳመጥ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የጀመሩትን ስራ በጊዜ በማጠናቀቅ ውጥረትዎን ይቀንሱ።

5. መጥፎ ግንኙነት ከመመሥረት መቆጠብ

ያለማቋረጥ ከሚያደናግር ሰው ጋር ግንኙነት ማድረግ ሳይታወቅ አንድ ሰው ለራሱ ከፍ ያለ ግምት ከማድረጉ ባሻገር በጭንቀትና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እንዲዋጥ ሊያደርገው ይችላል።

እንደዚህ ዓይነት ችግር በጓደኞችዎ እና በቤተሰብዎ ላይ መኖራቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ካነበቡ ቀርበው በማዳመጥ ጭንቀታቸውን መካፈል እና መፍትሄ በማምጣት ማገዝ አለብዎት።

6. በቂ እንቅልፍ ማግኘት

በቂ እንቅልፍ ካላገኙ ሰውነትዎ በትክክል ሊሠራ አይችልም።

ስለዚህ ለእንቅልፍ እየታገሉ ከሆነ፥ ለምን እንደዚያ እንደሆኑ በመንገር እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል።

Sleep-More.jpg

7. ለራስ ጊዜ ጊዜ መስጠት

በጓደኛ፣ በቤተሰብ እና በስራ መካከል ሁሉም ሰው ደስተኛ እንዲሆን በመፈለግ እራስዎን ችላ የሚሉ ከሆነ፥ ለራስዎ ምንም ጊዜ አልሰጡም ማለት ነው።

ስለዚህ ለራስዎ ጊዜ መስጠት ውጥረት እና የመንፈስ ጭንቀትን ለማስታገስ ይረዳል።

8. በዲጂታል መሳሪያዎች ብዙ ጊዜ አለማጥፋት

ስማርት ስልኮች፣ ታብሌቶች እና ላፕቶፖ ኮምፒውተሮች አዕምሯችንን ከመጠን በላይ ሊያስጨንቁ ይችላሉ።

ስለዚህ የአዕምሮዎን ጤንነት ማስቀጠል ከፈለጉ ቢያንስ ከግማሽ ቀን እስከ ሁለት ሰዓታት እረፍት መውሰድ ያስፈልጋል።

9. በርካታ ተግባራትን በአንድ ጊዜ ከመስራት መቆጠብ

በበርካታ ስራዎችን በአንድ ጊዜ መስራት የአዕምሮ ውጥረት ሊያመጡ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

ለዚህም በርካታ ተግባራት በአንድ ጊዜ ለማከናወን ከመሞከር ይልቅ እየሰራነው በሚገኘው አንድ ነገር ላይ ማተኮር የበለጠ ከአዕምሮ ውጥረት ያድናል።

overworked-businessman.jpg

ምንጭ፦ http://www.independent.co.uk