የእርድ ሻይ መጠጣት የሚያስገኛቸው የጤና በረከቶች...

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) እርድ በተለያዩ ሀገራት የሚገኝ ቅመም ሲሆን ህንድ 78 በመቶውን ምርት ለዓለም ታቀርባለች።

እርድ በተለያዩ ምግቦች ላይ በቀለም ማሳመሪያነት እና በቅመምነት የሚገባ ሲሆን በሻይ መልኩ መጠጣትም ይመከራል።

በየቀኑ መውሰድ ከሚገባን እርድ ውስጥ በሻይ መልኩ መጠጣታችን የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል።

1. የመገጣጠሚያ ህመምን ይቀንሳል።

2. የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል።

እርድ በውስጡ በያዘው የፀረ መርዛማነት፣ የፀረ ቫይረስ፣ እና የፀረ ባክቴሪያ ንጥረ ነገር አማካኝነት የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ያሳድጋል።

3. ለልብ ጤና ፋይዳው የላቀ ነው።

4. የካንሰር ህመምን ይከላከላል።

እርድ በውስጡ የፀረ ካንሰር ንጥረነገር ያለው በመሆኑ በቫይረስ አማካኝነት የሰውነት ህዋሳት እንዳይጎዱ ይከላከላል።

5. ለምግብ መፈጨት ያገለግላል

እርድ ለምግብ መፈጨት ጥቅም ስላለው ሰዎች ምግብ አልሀዋድ በሚላቸው ጊዜ በባህላዊ መንገድ ቤት ውስጥ ይጠቀሙታል።

6. ከፍተኛ የመርሳት ችግርን ለመከላከል እና ስጋቱን ለመቀነስ ያስችላል።


ጥናቶች እርድ ከተለያዩ አዕምሯዊ ጉዳቶች እንደሚከላከል እና የማስታወስ አቅምን እንደሚጨምር ያሳያሉ።

7. ጉበት እንዳይጎዳ ያደርጋል።

8. ከስኳር ህመም ይታደጋል።

9. ሳንባ እንዳይጎዳ እና አተነፋፈስ የተሻለ እንዲሆን ያግዛል።

ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎችን የጤና ጥቅምች የሚያስገኘውን የእርድ ሻይ ለማዘጋጀት የሚከተለውን አሰራር ይጠቀሙ።

አራት ብርጭቆ ውሃ ማፍላት፣

አንድ ወይም ሁለት የሻይ ማንኪያ የተፈጨ እርድን መጨመር፣

ውሃውን እና የተፈጨውን እርድ ለ10 ደቂቃዎች እንዲዋሃድ እና አብሮ እንዲፈላ ማድረግ፣

ከዚያ በመጠጫ ቀድቶ ለ5 ደቂቃዎች ማቀዝቀዝ እና የእርድ ሻይ ጣፋጭ እንዲሆንም ማር ጨምሮ በማዋሃድ መጠጣት ተገቢ ነው ተብሏል።

ሎሚ፣ ዝንጅብል፣ ወተት፣ ክሬም እና የኮኮናት ዘይትም ከእርድ ጋር ቢዋሃዱ መልካም መሆኑ ነው የተነገረው።

 

 

 

 

ምንጭ፦www.medicalnewstoday.com