የህንድ ዶክተሮች ከአንድ ወር ህፃን 7 ጥርስ አወጡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህንድ ዶክተሮች በምዕራብ ህንድ ጉጃራት ግዛት የአንድ ወር እድሜ ካለው ህፃን ሰባት ጥርስ አወጡ።
የሕፃኑ ጥርስ ከተወለደ ከጥቂት ቀናት በኋላ መታየቱ ተገልጸዋል።

ወላጆቹ ህፃኑ ጡት መጥባት ሲከብደው ወደ ህፃናት ሐኪም ቤት እንደወሰዱትም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ሀኪሞቹ በህፃኑ አፍ ውስጥ ነጫ ያልተለመደ ነገር ሲመለከቱ ወደ ከፍተኛ የህፃን ዶክተር እንደወሰዱት ነው የተገለፀው።

ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ቀዶ ጥገናው በሁለት ዙር የተፈፀመ ሲሆን፥ በመጀመርያው ዙር አራት ጥርስ እና በሁለተኛው ዙር ደግሞ ሶስት ጥርስ የማውጣት ሂደት ተከናውነዋል።

ከጥርሱቹ አንዳቸው ቢሰበሩ ህፃኑ በጉሮሮው ውስጥ ገብተው ችግር ስለሚፈጥሩለት ጥርሰ ነቀላው በጥንቃቄ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ ማስወገድ እንደተቻለ ተገልፀዋል።

በነሃሴ ወር ቀዶ ጥገናው ከተደረገለት በኋላ የህፃኑ ጤንነት በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሃኪሞቹ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ