ለቆዳችን ጤንነት የሚጠቅሙን 6 መሰረታዊ ነገሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 1፣ 2009፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰዎች ቆዳቸው ጤናማ ሆኖ ለመቆየት ምን እንደሚያስፈልግ ካለማወቅ ወይም ቸል ከማለት የተነሳ ይህ የሰውነት ክፍላቸው ሲጎዳ ይስተዋላል።

ለዚህ ደግሞ የቆዳ ጤና ባለሙያዎች የቆዳ ጤንነትን ለመጠበቅ የሚረዱ ስድስት ምክሮችን ያስቀምጣሉ።

1. የሞባይል ስልክዎን የፊት ገፅ በየጊዜው ያፅዱ


በሞባይል ስልክ ስክሪኖች ላይ ከመፀዳጃ ቤቶች በበለጠ በባክቴሪያ የተሞሉ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በመሆኑም ሰዎች በሞባይል ስልክ በሚነጋገሩበት ወቅት ጉንጫቸውን የሚነካው የሞባይል ስክሪን ላይ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ቆዳችንን ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ለሆድ እና ጨጓራ ህመም በማጋለጥ በአጠቃላይ ጤንነታችን ላይ ከባድ አደጋን ሊያስከትሉ ይችላሉ ነው የሚሉት።

ስለዚህም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች በመግዛት በትንሽ ጨርቅ እየነከሩ ዘወትር ስልክዎን ንጹህ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።

gallery-1473348390-cleaning-phone.jpg

2. በጣም በሞቀ ውሃ ሰውነት አለመታጠብ

ሰውነታችንን በምንታጠብበት ጊዜ የውኃ ሙቀት መጨመር ባክቴሪያዎች ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋቸዋል።

ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ባክቴሪያዎች በ140 ዲግሪ ፋራናይት ወይም ከዚያ በላይ ከፍ ባለ ሙቀት ባለው ውሃ ነው የሚሞቱ።

ይህም ከባድ ሙቀት ባለው ውሃ ሰውነትዎ ከታጠቡ ቆዳዎ ከማቃጠል ባሻገር የተፈጥሮ ዘይቶችን ከሰውነት ያስወግዳል ሲሉ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

እንዲሁም እንደ የቆዳ በሽታ፣ የስኳስ በሽታ፣ የአይን ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉ የቆዳ መቆጣት ችግሮች ሊፈጥር ይችላል።

ስለዚህም ለእንደነዚህ ያሉ ችግሮች እንዳይጋለጡ ለሰውነት ይሁን ፊትዎ የሚጠቀሙበት ውሃ ከልክ በላይ አለማሞቅ ይመከራል።

3. የሚጠቀሙባቸው የጥርስ ብራሾች በደምብ ማጠብ

በዓለም አቀፍ ብሩሽ ዲዛይን እና አምራች ኩባንያ አኒሳ ኢንተርናሽናል በተደረገ አንድ ጥናት መሰረት 20 በመቶ ከሚሆኑ ሴቶች አብዛኛዎቹ ግንዛቤ ከማነስ የተነሳ ብሩሾቻቸው ሳያጥቡ ይጠቀማሉ።

ይሁን እንጂ የጥርስ ብሩሽ፣ ስፖንጆች፣ ልብሶችን እና ምላጭዎችን ጨምሮ በፊትዎ ላይ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ማንኛውም ዕቃ ማፅዳትና ፀረ ባክቴርያ በመጠቀም መጥረግ እንዳለብን ተነግሯል።

አለበለዚያ ባክቴሪያዎች ከቆዳ ጋር በተደጋጋሚ መገናኘት ከመቻላቸው በላይ በዓይን ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ይህን ለማድረግ እውቀት እንኳን ብያጥረን በዩ ትዩብ የተጫኑ ቪድዮዎች ከፍተን በመመልከት እንዴት እቃዎቹ ማፅዳት እንዳለብን መማር እንችላለን።

gallery-1473341022-make-up.jpg

4. ከልክ በላይ ቆዳን አለማፅዳት

ቆዳዎን ማጽዳት በሰውነትዎ ላይ የተገነባውን የሞቱ ሕዋሳት እና ቆሻሻ ለማስወገድ ታላቅ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ከልክ በላይ መሆን የለበትም ሲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ። ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ ደጋግሞ ማጽዳት የቆዳ ሴሎች ለጉዳት ከማጋለጡ በላይ በቆዳዎ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

ይህም የቆዳ መድረቅ፣ መቅላት እና የቆዳ መቆጣት ወይም መኮማተር ያስከትላል።

ከሚገባ በላይ ደጋግመን ሰውነታችን በምናፀዳበት ጊዜም ከሌሎች የሰውነታችን ክፍል በበለጠ የሚጎዳው ፊታችን መሆኑ ተጠቁሟል።

ስለዚህ በጣም ብዙ ጊዜ ቆዳዎን ማፅዳት እንደሌለበዎት ይመከራል። ይህንን ምክር የማይተገብሩ ከሆነ ደግሞ እንደ አረንጓዴ ሻይ እና የመሳሰሉ ንጥረ ነገሮች የሚያካትቱ ምርቶችን መጠቀም አለበዎት።

5. ከእንቅስቃሴ በኋላ ሰውነታችንን መታጠብ

ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጋችን በኋላ ሰውነታችን መታጠብ ቆዳችን ጨምሮ ለሴሎቻችን እንቅስቃሴ እና ለደም ዝውውር አስፈላጊ ነው።.

ይህን ማድረግ የማይቻል ከሆነም የእጅ መታጠፍያ፣ የጉልበቶች ጀርባ፣ የሆድ እግር እና ብብት አካባቢ ቅድሚያ የሚሰጥባቸውን አካባቢዎች ለማጽዳት እርጥብ በሆነ የሰውነት ማፅድያ መጠቀም ያስፈልጋል ሲሉ ባለሙያዎቹ ምክር ሰጥቷል።

gallery-1473342720-woman-after-workout.jpg

6. የፊት ገፅታን መንከባከብ

ፊታዎ አንድ የሰውነትዎት ክፍል ነው፤ ለዚህ ክፍል የሚደርገው እንክብካቤም የላቀ መሆን አለበት።

ይሁን እንጂ ፊትዎን ከማለስለስና ከማፅዳት ይልቅ ችግር ያለባቸው (እብጠት፣ ብጉር ወዘተ) ቦታዎች የቆዳ ሀኪሞች በሚያዙት ተስማሚ መድሐኒት በመጠቀም ማከም ያስፈልጋል።

maxresdefault.jpg

ምንጭ፦ netdoctor.co.uk