ልጆች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሱስ ተጠቂ ሆነው እንዳያድጉ ለማድረግ የሚጠቅሙ 10 ተግባራት

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክሎጂ ውጤቶች ለልጆች የአዕምሮ እድገት ወሳኝ ጠቀሜታ ያላቸውን ያህል ጉዳት እንዳላቸውም የስነ ልቦና ምሁራን ይናገራሉ፡፡

ዶክተር ቪክቶሪያ ኤል ደንከሌይ ለረዥም ጊዜ በቴክኖሎጂ ስክሪን ላይ ማሳለፍ የመነቃቃት ጥገኝነትን ያመጣል ይላሉ፡፡

ጌሞችን የሚጫወቱበትን እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ምስል በስክሪን ላይ የሚመለከቱበትን ጊዜ መወሰን ካልተቻለ በልጆች አዕምሯዊ እድገት ላይ አሉታዊ ጫና ሊያስከትል እንደሚችል ነው ዶክተር ዱንክለይ የሚናገሩት፡፡

በተለይም የማህበራዊ ትስስር ገፆች ጫና ልጆች በብዛት ተቀምጠው እንዲሳልፉ እና ለውፍረት እንዲጋለጡ፣ ትምህራተቸውን በአግባቡ እንዳያጠኑ፣ በቂ እረፍት እንዳይወስዱ ወይም እንዳይተኙ እያደረገ መሆኑ ወላጆችን እያሳሰበ ይገኛል፡፡

በዚህም ምክንያት አንዳንድ ወላጆች የልጆች አስተዳደግን በሚመለከት የቤት ውስጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን የሚወስን ደንብ አውጥተው እየተገበሩ ነው፡፡

ልጆች ከቴክኖሎጂ ውጤት የሚያገኙት ጥቅምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አስተዳደጋቸውን መልካም ለማድረግ ወላጆች የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀማቸው ጠቃሚ ነው ተብሏል፡፡

1. ልጆች በቤት ውስጥ የኮምፒውተር፣ የቴሌቪዥን ወይም የስልክ ስክሪን የሚመለከቱበትን ጊዜ መወሰን

በዚህ ተሞክሮ ጥሩ ለውጥ ያገኙ ወላጆች እንደሚናገሩት ጧት ለግማሽ ሰዓት ማታም ለግማሽ ሰዓት ልጆች የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲጠቀሙ የማድረግ ልምድ አላቸው፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ የሚሰጣቸው ጊዜ ወደ 45 ደቂቃ ከፍ ይላል ነው ያሉት፡፡

በዚህም ልጆቻቸው የቤት ስራቸውን በመስራት፣ በማንበብ ጥሩ ውጤት ማስመዝገባቸውን ይናገራሉ፡፡

2. ግልፅ እና በአቋም ፅኑ መሆን

ስለ ልጆች አስተዳደግ ስኬታማነት ሲታሰብ በዓላማ ግልጽ መሆን እና ይጠቅማል በሚሉት አቋም ጽኑ ሆኖ ውጤቱን ማየት ተገቢ ነው፡፡

3. ከምፒውተሮችን ፣ቴሌቪዥን እና ስልኮችን መቆለፍ

አንዳንድ ጊዜ መጥፎ የባህሪ ለውጦችን ለመከላከል ልጆች ኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በቀላሉ እንዳያገኙ ማድረግ ጥቅሙ ከፍተኛ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

4. በልጆች ላይ ክትትል ማድረግ

ነገ መልካም ሰው ሆነው እንዲገኙ የምንፈልጋቸውን ልጆቻችንን የዕለት ውሎ በመከታተል ድክመቶችን መቅረፍ መልካም ነገሮችንም ማበራታት እንደሚስፈልግ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

5. የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአግባቡ አለመጠቀም ስላለው አደጋ ለልጆች ማሳወቅ

ልጆች ቴክኖሎጂ ስላስገኘላቸው አዳዲስ ነገሮች በማሰብ መጥፎ ጎኑን ላይገነዘቡ ስለሚችሉ ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀምን ተከትለው ጉዳት እንዳይደርስባቸው ማስገንዘብም ግድ ይላል፡፡

6. በአማራጭ ተግባራት ላይ እንዲያተኩሩ መገፋፋት

ታዳጊዎች በቤት ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ አማራጭ የመዝናኛ ወይም ስራ ጊዜ ላይራቸው ይችላል፡፡

በዚህ ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ከቴክኖሎጂ ውጤቶች ረዥም ጊዜ መጠቀም ለማውጣት እንደ አመቺነቱ አማራጭ የመዝናኛ እና ስራ ሁኔታዎችን ማፈላለግ አለባቸው፡፡

7. በየጊዜው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጉዳት እና ጥቅም ጋር የተገናዘቡ የእርምጃ ለውጦችን ማድረግ

ከልጆች እድገት ጋር የተገናዘቡ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጉዳት እና ጥቅም ስለሚኖር በየጊዜው አስፈላጊ የሆኑ የእርምጃ ለውጦችን ማድረጉ ወሳኝ ነው፡፡

8. ከቴክኖሎጂ ለተወሰነ ጊዜ ርቀው የሚዝናኑበትን ፕሮግራም ማመቻቸት

ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ ልጆችን በመዝናኛ ስፍራዎች ወስዶ ለተወሰነ ጊዜ በተፈጥሮ እና በሌሎች ሰው ሰራሽ መዝናኛዎች እንዲዝናኑ ማድረግ፣ ሙዚየሞችን ማስጎብኘት፣ የበጎ አድራጎት ስራ እንዲሰሩ ማድረግ ጥቅሙ ላቅ ያለ ነው ተብሏል፡፡

9. አርዓያ መሆን

ወላጆች የነገ ተተኪን ለመፍጠር፣ መልካም ዜጋን ለማፍራት በሁሉም ዘርፍ መልካም አርዓያ መሆን ይጋባቸዋል፡፡

በዘመናዊው ዓለም የልጆችን መብት በማይጋፋ መልኩ ቁጥጥር እያደረጉ፣ አካላዊ ቅጣት ሳይቀጡ በሰለጠነ እና ለሀገር መልካም ዜጋ መፍራት በሚቻልባቸው መንገዶች ማሳደግ ይገባል ይላሉ የማህበራዊ እና ስነልቦና ባለሙያዎች፡፡

 

 

 

ምንጭ፡- ሳይኮሎጂ ቱዴይ