በሕይወት የሚያጋጥሙ መጥፎ ስሜቶችን ከአዕምሮ ለማጥፋት የሚረዱ ስድስት ነገሮች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ሻክሮ መለያየት ይከሰትና በአዕምሮ ላይ መጥፎ አሻራ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡

ሰዎች በነበራቸው መልካም ግንኙነት ብዙ ነገሮች በአዕምሯቸው ቢቀመጡም መጥፎ ነገር አጋጥሞ በመካከላቸው መኮራረፍ ወይም መለያየት ሲከሰት መጥፎውን ስሜት ለማራቅ ይከብዳቸው ይሆናል፡፡

በመሆኑም ስሜቶቹን እንዳሉ ከማስተናገድ ይልቅ ለመቋቋም መሞከር ለምን እንደተከሰቱ ማጥራት እና በወደፊት ህይወት ላይ ጫና እንዳይፈጥሩ መገደብ ወሳኝ ነው፡፡

ሌሎች ሰዎች መጥፎ ስሜት የሚፈጥር ንግግር ወይም ተግባር ሲያንፀባርቁብን ይሉኝታ ይዞን በዝምታ ልናልፍ እና በአዕምሯችን ልንብሰለሰል እንችላለን፡፡

ታዲያ በአዕምሯችን ውስጥ መጥ ነገሮች ቦታ ይዘው ህይወታችን ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳርፉ የሚከተሉትን ገሮች ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡

1. በደልን በይሁንታ መቀበል

ከሰዎች ጋር በነበረ ጊዜ በርካታ የደስታ ጊዜ አልፎ መጥፎ ነገር የደረሰባቸው ሰዎች በአዕምሯቸው ላይ ቦታ እንዳይኖረው በደሉን ወይም ጉዳቱን ለበጎ ነው በሚል በይሁንታ መቀበል መልካም ነው፡፡

2. በስነልቦና ብርቱ መሆን

ሰዎች ማንኛውም ጥሩ ልሆነ ስሜት ሲከሰት ራሳቸውን ጠንካራ አድርገው ማሰብ በአዕምሮም መዘጋጀት ደስተኛ ህይወት እንዲኖራቸው ያግዛቸዋል፡፡

3. ከሌሎች ሰዎች ጋር መወያየት

በሕይወት ሂደት ውስጥ ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት የሚያሻክር ብሎም መለያየትን የሚፈጥር ነገር በሚፈጠርበት ጊዜ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስላጋጠማቸው ነገር ከሌሎች ሰዎች ጋር ቢያወያዩ ጥሩ ነው፡፡

ውይይቱም መጥፎ ትዝታዎችን የሚያስረሱ ምክሮችን ለማግኘት የሚረዳ ሲሆን፥ የወደፊት ህይወት በአሉታዊ አስተሳሰብ እንዳይመራ ብሩህ መንገድን ይፈጥራል፡፡

4. መጥፎው ስሜት በአካልና አዕምሮ ጤና ላ ቀውስ እንዳይፈትር መጠንቀቅ

በርካታ ተመራማሪዎች በአግባቡ መመገብ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መጥፎ ስሜትን ከአዕምሮ ለማጥፋት ወሳኝ ነገሮች መሆናቸው ላይ ይስማማሉ፡፡

እነዚህን ተግባራት በመተግበርም የአካልና የአዕምሮ ጤናን በመጠበቅ ጠንካራ ሰው መሆን ያስፈልጋል፡፡

በተለይም መጥፎ ስሜትን ለመቅረፍና ለአዕምሮ ጤና ተመስጦ ማድረግ፣ መልካም ነገሮችን ማሰብ እና ዮጋ ስፖርት ማዘውተር የተመከረ ሲሆን፥ መንፈስን ለማደስና አካልን ለማፍታታትም ወሳኝ መሆናቸው ነው የተጠቆመው፡፡

5. ጥፋቱ ሆን ተብ እንዳልተፈፀመ ማሰብ

የሰው ልጅ ስህተት ሊሰራ እንደሚችል መገመት፣ አንዱ አንዱን ለመጉዳት በሚል መጥፎ ነገር እንደማያደርግ አምኖ ቀበል መጥፎውን ነገር ከአዕምሮ ለማስወገድ ይረዳል፡፡

በመሆኑም ለጥፋቱ ይቅርታን መጠየቅና መቀበል፣ ሆን ብለው የማይገባ ንግግር ወይም ድርጊት እንዳልፈፀሙ ማረጋገጥ አዕምሯዊ ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡

6. በራሳችን መልካም መንገድ መጓዝ

ህይወት በውጣ ውረድ የተሞላች በመሆኗ እንቅፋት ባጋጠመ ቁጥር ማማረር እና ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡

በመሆኑም ከሰዎች ጋር ያለ ግንኙነት በአንደኛው ወገን ጥፋት ሲሻክር እና መራራቅ ሲያጋጥም፥ ጥፋቱን ያደረሰውን አካል መሸኘትና የራስን መልካም ጉዞ መጀመር ወሳኝ ነው፡፡

ይህን ማድረጉ ቀጣይ የህይወት አቅጣጫችን የተሳካና በመጥፎ ትዝታ እንዳይሞላ ያደርገዋል፡፡

ስለዚህ ሰዎች ሁሉ በህይወታቸው መጥፎ ነገር ሲያጋጥማቸው ፥በአዕምሯቸው ቦታ ሳይሰጡ መልካም ነገርን ሰንቆ አዲስ ህይወትን በብሩህ ተስፋ

መቀጠል ኖርባቸዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፡-ሳይኮሎጂ ቱዴይ