ተመራማሪዎች የተጎዳ የእግር ጉልበትን የሚተካ ሰው ሰራች ጉልበት በ3D ቴክኖለጂ መስራታቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተመራማሪዎች የተጎዳ የእግር ጉልበትን የሚተካ ሰው ሰራች ጉልበት በ3D ቴክኖለጂ መስራታቸውን አስታውቀዋል።

ከሰውነታችን ክፍል አንዱ የሆነው የእግራችን መገጣጠሚያ ጉልበት ላይ የስፖርት አሊያም በተለያዩ አደጋዎች እንዲሁም በእድሜ መግፋት አማካኝነት ጉዳት ሊደርስበት ይችላል።

ታዲያ ይህንን ጉዳት የደረሰበትን የመገጣጠሚያ አካል መልሶ ለመጠገን አሊያም በሌላ ለመተካት ተፈጥሮ ከለገሰችን ጋር ተመሳሳይና ጠንካራ የሆነ ምትክ ማግኘት አልተቻለም ነበር።

አሁን ግን ተፈጥሮ ከለገሰችን የእግራችን ጉልበት ጋር በጥንካሬው የሚቀራረብ ሰው ሰራሽ ጉልበት በተፈጥሮ መስራት መቻላቸውን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

ተመራማሪዎቹ በ3D ቴክኖለጂ በመታገዝ ከሀይድሮጄል ካርቲሌጅ (ለስላሳ አጥንት) መስራት የቻሉ ሲሆን፥ ይህም ጉዳት የደረሰበት የእግራችንን ጉልበት በንቅለ ተከላ ለመተካት የሚያስችል ነው ብለዋል።

ይህንን ግኝት በአሜሪካ የሚገኘው የዱክ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሲሆን፥ ለካስቲሌጅ (ለስላሳ አጥንት) መስሪያነት የሚያገለግለውን የሀድርጄል ግብአትም እዛው እንደሰሩ ተገልጿል።

ምንጭ፦ www.upi.com/Health