ተመራማሪዎች በእጅ የሚታሰር የበሽታ መቆጣጠሪያና መመርመሪያ መሳሪያ ሰርተናል እያሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ልክ እንደ ሰዓት እጅ ላይ የሚታሰር የተለያዩ በሽታዎችን መመርመር እና መቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ መስራታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

መሳሪያው በቆዳ ላይ ያለውን ላብ ወይም እርጥበታማ ነገር በመሰብሰብ የስኳር በሽታን፣ የጡንቻ ውጥረት እና ሌሎችንም በሽቻዎች ያሉበትን ደረጃ በመተንተን ያሳውቃል፡፡

መሳሪያው የሰውነት ክፍልን በማንበብ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ የክሎራይድ አዮኖችን እና የግሉኮስ ወይም የስኳር መጠንን ከለካ በኋላ የምርመራ ውጤቱን መነሻ በማድረግ

የጤና ሁኔታዎችን አስጊ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ወደ ስማርት ስልክ በማስገባት ያሳውቃል ተብሎለታል፡፡

ይህ መሳሪያ ከዚህ በፊት ከነበሩ የሰውነት ጤንነትን የመለኪያ መሳሪያዎች ለረጅም ጊዜ የሚጠይቁትን የምርመራ ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሳወቅ ይቀርፈዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መሳሪያው ሁለት ተጣጣፊ የሰውነት ላብ ማንበቢያ ወይም ማይክሮ ፕሮሰሰሮች ያሉት ሲሆን፥ ቆዳ ላይ በማድረግ ብቻ አንደኛው ሲለካ ሌላኛው ደግሞ ተንትኖ ከስማርት ስልክ ጋር በማገናኘት ውጤቱን ያሳውቃል፡፡

መሳሪያው ከፍተኛ የስኳር መጠን በሰውነታችን ውስጥ መኖሩን ከጠቆመ ለስኳር በሽታ ተጋልጠን ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው ብለዋል የስታንፎርድ ተመራማሪዎች፡፡

በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የማህበራዊ አገለግሎት ባልተሟላባቸው ገጠራማ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች የዚህ መሳሪያ ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡

 

 

 

 

 

 

www.gadgetsnow.com