ብጉንጅን በቤት ውስጥ በቀላሉ ለማከም…

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብጉንጅ በቆዳ ላይ በእብጠት መልክ በመውጣት ወደ ቁስልነት የሚቀየር ሲሆን፦ በተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ሊከሰት ይችላል።

ጉንጅ በሰውነት ላይ ከሚፈጥረው እብጠት እና የመቁሰል ምልክት በዘለለ የከፋ አደጋ ጉዳት እንደማያደርስም ነው የሚነገረው።

ሆኖም ግን አልፎ አልፎ የሰውነት ትኩሳት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ አይነት ምልክቶች ሊያሰከተል ይችላል።

ብጉንጅ የሰውነታችን አካል ላይ የመቆረጥ አደጋ ሲያጋጥም በሚፈጠር ቁስል ወይም በጭንቅላታችን ላይ ባለ የጸጉር መውጫ ቀዳዳ በኩል ወደ ሰውነታችን በሚገቡ ባክቴሪያዎች አማካኝነት ሊከሰት ይችላል።

ይህንን ችግር በቤት ውስጥ በሚዘጋጁና ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ለማከም የሚረዱ ዘዴዎችን እነሆ ብለናል።

ኦ.አር.ኤስ ወይም በተለምዶ የእንግሊዝ ጨው

በሙቅ ወይም ለብ ባለ ውሃ ውስጥ ኦ.አር.ኤስ ወይም በተለምዶ የእንግሊዝ ጨው በመባል የሚታወቀዉን በመጨመር በሚገባ ከደባለቅን በኋላ ሰውነታችንን በውሃው መታጠብ ከብጉንጅ በቀላሉ ሊፈውሰን ይችላል ይላሉ ተመራማሪዎች።

ዳቦ

ዳቦ ብጉንጅን ለማጠፋት ፍቱን ነው የተባለለት ሲሆን፦ ለብ ያለ ውሃ ወይም ወተት ካዘጋጀን በኋላ ዳቦውን እዛ ውስጥ ጨምረን በማዋሃድ ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ በቀን ሁለት ጊዜ በመቀባት ራሳችንን በቀላሉ ማከም እንችላለን።

ነጭ ሽንኩርት

ለብዙ ህመሞች ፈዋሽ መሆኑ የሚነገርለት ነጭ ሽንኩርት ብጉንጅን ለማከምም ጠቀሜታ እንዳለው ነው የሚነገርለት።

ብጉንጅን ለማከም በመጀመሪያ ነጭ ሽንኩርቱን በእሳት ላይ ሞቅ እንዲል በማድረግ ይጠበቅብናል።

በመቀጠልም ጉንጁ ባለበት ቡታ ላይ በማድረግ ለ10 ደቂቃ ያክል ማቆየት፤ ይህንን ለተወሰኑ ቀናት ደጋግሞ በመጠቀም ለውጥ ማግኘት የቻላል ተብሏል።

እንቁላል

እቁላልን ከቀቀልን በኋላ ነጩን ክፍል በማንሳት በደንብ እንዲረጥብ በማድረግ ብጉንጁ ባለበት ቦታ ላይ ማድረግ፤ ከዚያም በንጹህ ጨርቅ አስረን ማቆየት ሌላኛው በቀላሉ በጉንጅን ለማከም የሚረዳን ዘዴ ነው።

ወተት

ወተት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ብጉንጅን ለማከም በጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።

በአንድ ብርጭቆ ወተት ውስጥ ሶስት የሻይ ማንኪያ ጨው እና የሰንዴ ዱቄት ከጨመርን በኋላ አንድ ላይ በመደባለቅ ከዚያም ለተወሰኑ ቀናት በየቀኑ ደጋግመን ቦታው መቀባት ብጉንጅን ለማከም ፍቱን ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ healthdigezt.com


በሙለታ መንገሻ

android_ads__.jpg