በ2030 በየአመቱ ትንባሆ በማጨስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 8 ሚሊየን ይደርሳል - የአለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትንባሆ ከማጨስ ጋር ለተያያዙ ችግሮች በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ 1 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ይደረጋል ተባለ።

የአለም ጤና ድርጅት እና የአሜሪካ ብሄራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ባደረጉት ጥናት መሰረት፥ በፈረንጆቹ ከ2030 ጀምሮ በየአመቱ በትንባሆ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 8 ሚሊየን ይደርሳል።

የአለም ሀገራት ከማጨስ ጋር ለተያያዙ ችግሮች የሚያወጡት ወጪ ከትንባሆ ቀረጥ ከሚገኘው ገቢ በእጅጉ የበለጠ ነው ብሏል ጥናቱ።

ለአብነትም በ2013/14 ከትንባሆ ምርቶች ቀረጥ የተገኘው ገቢ 269 የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ነው የአለም ጤና ድርጅት የጠቆመው። ይህም ከወጪው አንፃር በጣም አነስተኛ መሆኑን ገልጿል።

ከትንባሆ ጋር በተያያዙ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ2030 ከ6 ሚሊየን ወደ 8 ሚሊየን ያድጋል፤ ከ80 በመቶ በላይ የችግሩ ሰለባ የሚሆኑትም መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ይሆናሉ ነው ያለው ጥናቱ።

ከ70 በላይ ተመራማሪዎች የተገመገመው ጥናት በአለም አቀፍ ደረጃ የአጫሾች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን ጠቁሟል። 


 ሲጋራ ማጨስ ስናቆም እነዚህን እናተርፋለን 


ትንባሆ በአለም ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሁንም ይቀጥላል ያለው ጥናቱ፥ ሀገራት የትንባሆ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እና ተያይዞ የሚከሰተውን የሞት መጠን ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን መቀየስ ይኖርባቸዋል ብሏል።

ባለ 688 ገፅ የጥናት ውጤቱ መንግስታት የትንባሆ ቁጥጥር ማድረግ በኢኮኖሚያችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል የሚለው ፍራቻቸው ተጨባጭ ምክንያት እንደሌለውም አብራርቷል።

በትንባሆ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ታክስ መጣል እና ዋጋቸውን ማስወደድ፣ ማጨስን የሚከለክሉ ፖሊሲዎችን ማውጣት፣ የትንባሆ ምርቶች ማስታወቂያን መከልከል እንዲሁም የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን ማስፈር የአጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ ይረዳሉ ተብለው ተጠቅሰዋል።

ከትንባሆ ምርቶች ቀረጥ ከሚገኘው ገንዘብ ውስጥም በመገናኛ ብዙሃን ለሚደረጉ የፀረ ትንባሆ እንቅስቃሴዎች ማዋል ይገባል ነው ያለው።


በሲጋራ ጭስ የተጎዳን ሳንባ ለማከም  


የጤና ባለሙያዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በትንባሆ ምክንያት እየተከሰተ ያለውን የሞት መጠን መቀነስ ወይም ማቆም ቀላል መሆኑን ይናገራሉ። ማጨስ በማቆም…

 

ምንጭ፦ ሬውተርስ

 


በፋሲካው ታደሰ

 

android_ads__.jpg