ሲጋራ ማጨስ ስናቆም እነዚህን እናተርፋለን

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እድሜን በጣም በአጭሩ የሚያስቀረውን ሲጋራ ለማቆም ብዙ ሰዎች የተለያዩ ጥረቶችን ያደርጋሉ።

አንዳንዶቹ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ ወደ ጤናማው ህይወታቸው ሲመለሱ፥ በቁርጠኝነት ማጣትም ይሁን በሌላ በዚሁ ሱሳቸው የሚቀጥሉም አሉ።

ሲጋራን በአንድ ጊዜ ወስኖ ከማቆም ቀስ በቀስ እየተለማመዱት ማቆሙ የተሻለ ነው የሚለው ሀሳብም ከሱስ የመውጣቱን ሂደት እንደሚያዘገየው ይታመናል።

ሲጋራ ማጨስን ለማቆም ያሰቡ ሰዎች ከሳንባ ካንሰር ጀምሮ የሚያስከትላቸውን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች መለስ እያሉ ቢያስቡ መልካም ነው።

አጫሾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሀሳቦች ቢመለከቷቸውና ባለሙያዎችን ቢያማክሩ በፍጥነት ከሱሳቸው ወጥተው ጤናማ ህይወት መምራት ይችላሉ ብሏል ሰርጊዮን ጀነራል ያወጣው ሪፖርት።

ሲጋራ የማቆም ጥቅሞች

1. ጥሩ እንቅልፍ

ሲጋራ በያዘው የኒኮቲን ይዘት የተነሳ የማነቃቃት ባህሪ አለው።

ስለሆነም ከመኝታ ስአታችን ከ1 ወይንም ሶስት ስአት በፊት ካጨስን የልብ ምታችን ከወትሮው በተለየ ፍጥነቱን ይጨምራል።

ይህም በቂ እንቅልፍ እንዳይወስደን ያደርጋል።

በመሆኑም ከሲጋራ የፀዳ ቀን ለጥሩ እንቅልፍ ወሳኝ ነውና ማጨስ ያቁሙ ይላሉ ተመራማሪዎች።

2. የተሻለ ማዕዛ ይኖረናል።

3. የማሽተት እና የመቅመስ ስሜታችን ያድጋል።

4. የሳንባ ጤናን ይጠብቃል፤ ሳል ይቀንሳል።

5. ራስን የመቆጣጠር ልዩ ብቃትን ያጎናፅፋል።

6. ሀይል እና ብርታት ይጨምራል።

7. የወትሮ ድምፃችን መልሶ ለማግኘት ይረዳል።

8. በራስ የመተማመን ስሜትን ያሳድጋል፤ ከሰዎች ጋር ለመቀራረብ እና አብሮ ለመስራት የሞራል ስንቅ ይሆናል።

9. ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ ያስችላል።

10. በአልባሌ ስፍራዎች ጊዜያችንን ከማሰለፍ ይታደጋል።

 

 

 

http://loveinspireamaze.com/

 

 

 

 


በፋሲካው ታደሰ