ለማብረር ፈቃድ የማያስፈልጋት በራሪ መኪና ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ለማብራር ፍቃድ የማያስፈልጋት በራሪ መኪና በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሙከራ ማድረጓ ተገለፀ፡፡

ብላክፍላይ የሚል ስም የተሰጣት በራሪ መኪና በ62 ኪሎ ሜትር ፍጥነት 40 ኪሎ ሜትር መብረር እንደቻለች ተነግሯል፡፡

በራሪዋን መኪና በሂደት የስፖርት መኪናዎቹ የሚያወጡትን ዋጋ የምታወጣ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ምርቶች ለማግኘት ግን ከፍተኛ ዋጋ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በአሁን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ኩባንያዎች በራሪ መኪናዎችን ለማምረት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በራሪዋ መኪና አንድ ሰው በመያዝ ሙከራ እንዳደረገችና መኪናዋን ለማንቀሳቀስ ኤይት ፕሮፕሉዚን የተባለ ስርዓትን እንደተጠቀመች ታውቋል፡፡

የአብራሪ ፈቃድ የማያስፈልጋት በራሪዋ መኪና በእሳር ላይ ለማኮብኮብም ሆነ ለማረፍ የምትችል በመሆኑ ተመራጪ አድርጓታል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ