ፌስቡክ በብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል የ500 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ተጣለበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል በፌስቡክ ላይ የ500 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ተነግሯል።

ማእከሉ በፌስቡክ ላይ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው ኩባንያው የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ መጠበቅ ላይ ክፍተት አሳይቷል በሚል ነው።

የኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ፌስቡክ ካንብሪጅ አናላቲካ የሚባለው ድርጅት የተደንበኞቹን መረጃ እንዲወድስ አድርጓል፤ አሁን ደግሞ ኩባንያው መረጃውን ማጥፋቱን ሊያረጋግጥ አልቻለም ነው ያለው።

ቢሮው ፌስቡክን ከመቅጣት በተጨማሪም የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ ያለአግባብ ተጠቅሟል በተባለው ካንብሪጅ አናላቲካ በተባለው ኩባንያ ላይም የወንጀለኝነት ክስ እንደሚመሰርትም አስታውቋል።

ፌስቡክ ከኩባንያው የተጣለበትን ቅጣት አስመልክቶ በቅርቡ ምላሽ እሰጣለው ከማለት ውጪ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበቧል።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ ያለፍቃድ እና ያለአግባብ አፕልን ጨምሮ ለሌሎች የቴክኖሎጂ መገልገያ አምራች ኩባንያዎች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ክስ ቀርቦበት እንደነበረም ይታወሳል።

ክሱን ኒው ዮርክ ታይም ጋዜጣ ያቀረበበት ሲሆን፥ ፌስቡክ ግን በክሱ ላይ የቀረበው መረጃ እውነት አይደለም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎታል።

ፌስቡክ ከዚህ ቀደምም ካምብሪጅ አናላቲካ የተባለው ተቋም የ87 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን መረጃ አላግባብ እንዲበረብር አድርጓል የሚል በምርመራ ስር እንደሚገኝ አይዘነጋም።

ምንጭ፦ www.bbc.com