ተስላ ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በሻንጋይ ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ03፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተስላ የተባለው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ ሊፍት ነው ተብላል።

ኩባንያው ከሻንጋይ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ሊንጋንግ በተባለው አካባቢ የተሽከርካሪ ፋብሪካውን ለመገንባት መፈራረሙም ታውቋል።

ኩባንያው በቻይና ፋብሪካውን ለመክፈት ያቀደው በኤለክትረክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በቻይና ሰፊ ገበያ እንዳላቸው በማረጋገጥና አሁን ላይ አሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣሏን ተከትሎ ተሽከርካሪዎቹን በተወዳደሪ ዋጋ በቻይና ገበያ ላይ ለማቅረብ ነው ተብሏል።

ተስላ ኩባንያ ከዚህም ሌላ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ በአውሮፓም ቅርጫፉን የመክፈት ፍላጎት እንዳለው ተመላክቷል።

 

ምንጭ፦ reuters.com and bloomberg.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ