ፌስቡክ የአሜሪካ ነፃነት ሰነድን የጥላቻ ንግግር የያዘ ነው በማለት ከገፁ በማንሳቱ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 28፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የአሜሪካ ነፃነት ሰነድን ጥላቻን ያዘለ ፁሁፉ ነው በማለት ከገፁ እንዳነሳው ተገለጸ፡፡

የአሜሪካን የነፃነት አስመልክቶ በቴክሳስ የሚገኝ አንድ ጋዜጣ በፌስቡክ ገፁ የአሜሪካ ነፃነት ሰነድን መለጠፉን ተከትሎ ነው ይህ ሁኔታ የተፈጠረው፡፡
ፌስቡክም ከቆይታ በኃላ ይቅርታ በመጠየቅ የነፃነት ሰነዱ በገጹ እንዲለጠፍ መፍቀዱ ተነግሯል፡፡

ይህን የነፃነት ሰነድ በፌስቡክ መለጠፍ ያስፈለገው በአንባቢዎች ላይ የታሪክ ስነፅሁፍን ለማበረታት ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ጋዜጣውም ፌስቡክ ከቆይታ በኃላ አቋሙን እንደቀየረ እና ይቅርታ መጠየቁን አረጋጧል፡፡

ፌስቡክ ስህተት መስራቱን እና ከገፁ ያነሳው ጉዳይ ከማህበረሰቡ አስተሳሰብ የተለየ እንዳልሆነ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ለዚህ ጉዳይ መፈጠር የጥላቻ ፁሁፎችን ለመለየት የተዘጋጀው ሮቦት እንደሆነ እና እነዚህ ሮቦቶች የፓለቲካ ቋንቋ መረዳ ችግር እንዳለባቸው ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ