ናሳ ያለአብራሪ የሚበር አውሮፕላን የተሳካ ሙከራ ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ፣ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ናሳ ሙሉ በሙሉ የመንገደኞች አውሮፕላን ቅርፅና መጠን ያለው እና ያለ አብራሪ የሚበር አውሮፕላን የተሳካ ሙከራ ማድረጉን አስታወቀ።

ኢልካና የተባለው ያለአብራሪ ሰዎችን ማጓጓዝ የሚችለው አውሮፕላን ከአሜሪካ አቪየሽን አስተዳደር ባገኘው ፍቃድ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ የበረራ አየር ክልል ሙከራ ማድረጉ ታውቋል።

ታሪካዊ ነው የተባለው ያለአብራሪ የሚበረው አውሮፕላን ሙከራ አሜሪካ እነዚህ የንግድ እና የግል አውሮፕላኖች በአየር ክልሏ እንዲበሩ እድል የሚያገኙበት ነው ተብሏል። 

ለመጀመሪያ ጊዜ ያለአብራሪ ሙከራ ያደረገውን ይህን አውሮፕላን ከምድር ሆነው በረራውን የሚቆጣጠሩ አብራሪዎች የተሳተፉበት እና የመጠቀ የቴክኖሎጂ ስርዓት ተዘርግቶለት የተከናወነ ነው ተብሏል።

ይህ ስርዓት የአውሮፕላኑን አቅጣጫ የሚመራ እና በበረራ ወቅት የሚከሰቱ የአየር ፀባይ ችግሮችን መከላከል የሚያስችሉ ነው ተብሏል።

ያለአብራሪ የሙከራ በረራውን ያደረገው ይህ የመንገደኞች አውሮፕላን በንግድ አውሮፕላን የአየር ክልልውስጥ በ6 ሺህ 100 ሜትር ከፍታ ላይ በሯል።

ናሳ አውሮፕላለኑን ወደ ፊት የደን እሳት ቃጠሎን ለመከላከል፣ ለድገተኛ ነፍስ አድን እና ፍለጋዎች ስራ ለማዋል ፍላጎት እንዳለው ተመልክቷል።

ምንጭ፡-ሲኤንኢቲ