አፕል የአይፎንን ሴቲንግ መቀየሩ አስታወቀ

አዲስአበባ፣ ሰኔ 7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዋና መቀመጫውን በካሊፎርኒያ ያደረገው ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል የአይፎን መመሪያ ሴቲንጉን መቀየሩ አስታወቀ፡፡

አፕል ይህንን ያደረገው ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው መረጃ የሚበረብሩ አካልትን ለማስቆም መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ለውጥ የአሜሪካ ፌደራል ምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይ ከዚህ ቀደም እንደሚበረብረው ለማድረግ ፈተና ይሆንበታል ተብሏል፡፡

የአፕል ኩባንያ በአሜሪካ ህግ አርቃቂዎች ዘንድ እየቀረበ ያለውን የተጠቃሚዎችን መረጃ ማየት የሚያስችለውን ህግ ከሚቃወሙት መካከል ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለውጡን ተከትሎ ታዲያ አፕል የአሜሪካ የህግ አስፈጻሚ አካላት የሚሰሩትን ስራ ለማደናቀፍ ያደረኩት አይደለም ብሏል፡፡

አፕል በመግለጫው ሴቲንጉን የቀየረው ከመረጃ በርባሪዎች የደንበኞቹን ደህንነት ለመጠበቅ ስራውን ማጠናከሩን አስታውቋል፡፡

በ2016 በካሊፎርኒያ 14 ሰው ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ኤፍቢአይና አፕል ኩባንያ ውዝግብ ውስጥ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

ውዝግቡም የጥቃት አድራሹን አይፎን ፖሊስ እንዲከፈትለት ለኩባንያው የጠየቀ ሲሆን፥ አፕል በበኩሉ ፍቃደኛ አልሆነም በዚህም ኤፍቢአይ የጥቃት አድራሹን ስልክ ለማስከፈት ከ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ ማውጣቱ ተገልጿል፡፡

 

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ