በቻይና የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያለው ላብራቶሪ ተከፈተ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራስ የማሰብ አቅም ባላቸው መሳሪያዎች የሚመራ የላብራቶሪ ማዕከል ተከፈተ፡፡


ማዕከሉ የተቋቋመው በጓንዡ የእናቶችና የህጻናት ሆስፒታል ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

ህክምና የሚያስፈልገው ግለሰብ የሚሰማውን የህመም ምልክት ወደ ማዕከሉ በድምጽ ወይንም በጽሁፍ መልዕክት ወደ ተዘረጋው ስርዓት ይልካል፡፡

ስርዓቱም የሚሰማውን የምልክት ዓይነት በመለየት የትኛውን ሐኪም መጎብኘት እንዳለበት ጥቆማ ይሰጣል፡፡

ስርዓቱም የመጀመሪያ ጎብኝና አዲስ ጎብኚም ለይቶ ያውቃል፤ በተጨማሪም ነባር ጎብኚዎችን መጀመሪያ ክትትል ወደ አደረጉበት ሐኪም መልሶ ይልካል ተብሏል፡፡

የሙከራ ፕሮግራም ባካሄደባቸው ባለፉት ሦስት ወራት በየዕለቱ 2 ሺህ ሰዎችን አስተናግዷል፡፡

የተነገሩትን የህመም ምልክቶች ለይቶና አውቆ በመላክ 94 በመቶ ስኬታማ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

ምልክቶቹን ደግሞ መነሻ በማድረግ ወደ ሚመለከተው ሐኪም በመላክ 96 በመቶ ተሳክቶለታል፡፡

እናቶችንና ህጻናትን የሚያጠቁ መደበኛ በሽታዎችን ጨምሮ 518 የሚደርሱ የህመም ዓይነቶችን የመለየት አቅም አለው፡፡

የሆስፒታሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ዲያንግ ኬይ ይህ ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያለው ስርዓት ገና ጅምር መሆኑን ጠቅሰው፥ ወደፊት አገልግሎቱ እንደሚስፋፋ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ሳይንስቴክ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ