የአፍሪካ ተመራማሪዎች አህጉር በቀል የሆኑ ዕውቀቶችን ከዘመናዊው ጋር እንዲያጣምሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ህብረት ለተመራማሪዎች አህጉር በቀል የሆኑ ዕውቀቶች ላይ አተኩረው ከስነህይወት ሳይንስ ጋር አጣምረው እንዲሰሩ ጥሪ አቀረበ፡፡

የህብረቱ ቴክኖሎጂ ክፍል ስራአስኪያጅ የሆኑት ይሳዬ ጋሳማ የአህጉሪቷ የዘረመል ሀብት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ አለበት ብለዋል፡፡

እንዲሁም ቱባ የሆነውን ባህላችን መነሻ በማድረግ አስተማማኝ የሆነ ለውጥ፣ ሃብትና ብልጽግናን ማምጣት እንደምንችል እናስብ ብለዋል ጋሳማ፡፡

ጋሲማ ለስራ ፈጠራም ይሁን ስነምህዳሩን ለመጠበቅ ሲባል አህጉሪቷ ቴክኖሎጂን በማዘመን ወደ ባዮ-ኢኮኖሚ መሸጋገር እንዳለባት አጽንዖት ሰጥተው አንስተዋል፡፡

ባዮ ኢኮኖሚ መፍጠር ሲባል 90 በመቶውን የዓለም የነዳጅ ኢኮኖሚ በሌሎች ስነ ህይወታዊ በሆኑ ነገሮች መተካትና እንደ ባዮ ጋዝ የመሳሰሉትን የሚያካትት ነው፡፡

በተጨማሪም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ስነምህዳሩን የሚጠብቁ ከተክሎችና ከእንስሳት የሚገኙ ምርቶች ኬሚካላዊ ይዘት ያላቸውን ምርቶች እንደሚተኩ ገልጸዋል፡፡

በኬንያ የወጣቶችና የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር ማርጋሬት ካሬምቡ ሳይንሳዊ ምርምር ላይ በማተኮር የምግብ እጥረትንም መጋፈጥ ይቻላል ብለዋል፡፡

 


ምንጭ፦ሽንዋ