በአሜሪካ የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሙከራ ሊጀምሩ ነው

አዲስአባባ፣ ግንቦት 3 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በሰብል፣ በወባ ቁጥጥር እና በመድሃኒት አቅራቢነት አገልግሎት የሚሰማሩ ሰው አልባ የንግድ አውሮፕላኖች ሙከራ ሊጀምሩ ነው።

ለዚህም 10 ሰው አልባ የንግድ አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ሰማይ ሙከራ እንዲያደርጉ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ታውቋል::

በሙከራው በሩዋንዳ በደም አቅራቢነት የተሰማራው ዚፕሊኔ እና አፕል ኩባንያ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ተነግሯል።

ሆኖም በሰው አልባ አውሮፕላን ለደንበኞቹ የተለያዩ ቁሳቁችን ለማድረስ ፍላጎት ያሳየው አማዞን ፍቃድ አልተሰጠውም ተብሏል።

የሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንም ከዚህ በፈት በሰው አልባ አውሮፕላኖች አጠቃቀም ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዳለው ይነገራል።

ሙከራው የተፈቀዳለቸው ሰው አልባ የንግድ አውሮፕላኖች ከእይታ እንዳይርቁ እና በምሽት በረራ እንዳደርጉ መከልከላቸው ተገልጿል።

በአሜሪካ ህጋዊ ፈቃድ የወሰዱ እና የተመዘገቡ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 90 ሺህ አብራሪዎች ይገኛሉ ተብሏል።

የሰው አልባ አውሮፕላን አገልግሎት የሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይጥል እና ከሀገሪቱ የበረራ አገልግሎት ጋር እንዳይጋጭ የሚያደርግ ፕሮግራም መቀረፁም ተነግሯል።

 

 

ምንጭ፡- ቢቢሲ