የላፕቶፕዎን ንጽህና በዚህ መልኩ ይጠብቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዘያ 9 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የላፕ ቶፕ ኮምፒውተሮች ከቦታ ቦታ በብዛት እንደ መዘዋወራቸው መጠን ብናኝ ነገሮች፣ አቧራ እና ጀርም የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

ይህን ማጽዳት ቀላል ቢሆንም ከስሪታቸው አንጻር ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል፤ የላፕቶፑን ስክሪን ወይም ቁልፎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋልና።

ከዚህ አንጻር ላፕቶፖችን ከማንኛውም ብናኝ ቆሻሻ እና ጀርም የጸዱ እና ንጹህ ለማድረግ እነዚሀን መንገዶች ይከተሉ።

በቅድሚያ ላፕቶፑን ማጥፋትና ሶኬቶችን መነቃቀልዎን አይዘንጉ፤

ለማጽዳት የሚያስፈልጉ ነገሮች፤

በደንብ የተጣራ ንጹህ ውሃ፣ ነጭ ኮምጣጤ፣ አነስተኛ የመርጫ ፕላስቲክ፣ አነስተኛ መጠን ያላቸው ማጽጃ ፎጣዎች እና ከጥጥ የተሰራ የጆሮ ኩክ ማውጫ። 

plastic_spray.jpg

አጠቃቀም፥ በቅድሚያ ውሃውን ከነጩ ኮምጣጤ ጋር በእኩል መጠን በመርጫ ፕላስቲኩ ውስጥ መቀላቀል፤

የቀላቀሉትን ውህድ በማጽጃ ፎጣው ላይ መርጨት እና ማዘጋጀት፤

ላፕቶፑን ማጽዳት ከመጀመርዎ በፊት ብናኝ አቧራዎችን ከክፍል ውጭ ማራገፍ ያስፈልጋል።

ከዚያም በአንደኛው የፎጣ ጫፍ ላፕቶፑን በማጠፍ ውጫዊ ክፍሉን መወልወል።

በመቀጠል በፎጣው ሌላኛው ክፍል የላፕቶፑን ስክሪን በጥንቃቄ መወልወል፤ በዚህ ጊዜ ሃይል መጠቀም እና ጫን ማለት ጉዳት አለውና በስሱ ያድርጉት።

ከዚህ ባለፈም አልኮልም ሆነ ሌላ ኬሚካል በዚህ ጊዜ መጠቀም የላፕቶፑን ስክሪን ከጥቅም ውጭ ስለሚያደርገው እንዳይጠቀሙ።

ከዚህ በኋላ ደግሞ በሌላ ፎጣ ወይም ባላጸዱበት በኩል ውህዱን በመርጨት፥ የላፕቶፑን ጫፍ (ከስክሪኑ በላይ እና በታች ያለውን ክፍል) በስሱ መወልወልና ማጽዳት።

የላፕቶፑን ቁልፎች ለማጽዳት፥

ያዘጋጇቸውን ከጥጥ የተሰሩ ማጽጃዎችን ውህዱ ውስጥ መንከር እና ማውጣት።

ከዚያም በእያንዳንዱ የላፕቶፕ ቁልፍ መሃል በማስገባት መወልወል እና ማጽዳት፤ ሃይል መጠቀም አይመከርም።

ላፕቶፑን አጽድተው ከጨረሱ በኋላ በተዘጋጀ ደረቅ ፎጣ በስሱ መወልወል አይዘንጉ፤ ይህ መሆኑ ምናልባት ላፕቶፑ ላይ የቀረ ፍሳሽ ካለ ለማስወገድ ይረዳወታል።

ይህን መሰሉን ጽዳት በሳምንት አንድ ቀን ቢያደርጉት ደግሞ ይመከራል።

 

 

 

ምንጭ፦ www.ehow.com

በድጋሚ የተጫነ