በዩ ትዩብ ላይ በርካታ ተመልካች ያገኙ ቪዲዮዎች መጠለፋቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ ጠላፊዎች በዩ ትዩብ ላይ ተጭነው በርከካታ ተመልካቾችን ያገኙ ቪዲዮዎችን መጥለፋቸው ተነግሯል።

በመረጃ ጠላፊዎች እጅ ከወደቁት ውስጥም ከ5 ቢሊየን በላይ ተመልካች ያገኘው ዴስፓሲቶ የተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮ አንዱ መሆኑም ታውቋል።

የሚዚቃ ቪዲዮው በሚከፈትበት ጊዜም በቪዲዮው ላይ ላይ በሚመጣው የሽፋን ፎቶ ግራፍ ጭንብል ለብሰው የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ምስል መሆኑ ነው የተነገረው።

you_tube_b.jpg

በአሁኑ ወቅትም ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ቪዲዮው ከዩ ትዩብ ገፅ ላይ እንዲወርድ መደረጉም ታውቋል።

ከዲስፓሲቶ በተጨማሪም የሻኪራ፣ ሰሊና ጎሜዝ፣ ድሬክ እና ተይለር ስዊፍትን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ አርቲስቶች የሙዚቃ ቪዲዮዎችም የመረጃ ጠላፊዎቹ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል።

ራሳቸውን “ፕሮሰክስ” እና “ኩሮኢሽ” ብለው የሚጠሩት ጠላፊዎቹ የቪዲዮዎቹን ርእስ በራሳቸው መልእክት የተኩ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ “ነፃ ፊሊስጤም” የሚል ይገኝበታል።

ዩ ትዩብም እንዚህን ነገሮች በገፁ ላይ እንደተመለከተ በርካታ ቪዲዮዎችን በገፁ ላይ ከሚጭነው ቪቮ ጋር በመሆን ሙዚቃዎቹ እንዲወርድ ማድረጉን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ነው ዩ ትዩብ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ www.bbc.com