ዩ ትዩብ ህፃናትን የሚያስጨንቁ ቪዲዮዎችን ሊገድብ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩ ትዩብ ህፃናትን ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ለሁከት የሚያነሳሱ ናቸው ተብለው አስተያየት የተሰጣባቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሊዘጋ መሆኑን አስታወቀ።

ባለፈው ሳምንት ጀምስ ብሪድል የተባለ አንድ ጸሐፊ፥ ዩ ትዩብ ህፃናት ላይ ባተኮሩ ያልተለመዱ እና አግባብነት በሌላቸው ቪዲዮዎች ለችግር እየተጋለጠ መሆኑን ጠቁሟል።

ዩ ትዩብ በበኩሉ እንደዚህ አይነት ቪዲዮዎች ቀደም ሲል ከማስታወቂያ ያገኙት የነበረው ገቢ እንደቆመባቸው አስታውቋል።

የዩ ትዩብ ቡድን መተግበሪያው እንዲሻሻል እና በመተግበሪያው ላይ መብት ባላቸው ቤተሰቦች ላይ የተቋቋመ መሆኑንም አስታውቋል።

ተቺዎች በበኩላቸው ዩትዩብ ተመልካቾች አግባብነት የሌላቸው ቪዲዮዎች አስመልክተው የሚሰጡት ሪፖርቶችን በማየት በቂ እርምጃዎች እየወሰደ አይደለም ይላሉ።

ለዚህ እንደማሳያም የፊልም ሰሪዎችን ህጻናትን ለማስፈራራት እንደ ፔፓ ፒንግ( Peppa Pig)የመሳሰሉ ታዋቂ ገጸ ባህሪዎችን በመጠቀም ህፃናትን ብጥብጥ ወይንም ወሲብ የሚያስተምሩ ቪድዮዎ በስፋት ሪፖርት መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ብዙዎቹ እንደ ስፓይደርማን እና ኤልሳ የመሳሰሉት የቤተሰብ መዝናኛ ገጸ ባህሪያት በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጊዜያት መታየታቸው ተጠቁሟል።

ይሁንና ለህጻናት ተገቢ ያልሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በገጹ መኖራቸውን ተመልካቾች ሪፖርት ካደረጉ፥ በአስተያየቱ መሰረት ከእንደዚህ ያሉ ቪዲዮዎችን የሚገኝ የማስታወቂያ ገቢ በማስቆም ቪድዮዎቹን እንደሚያስወግድ አስታውቋል።

ዩ_ትዩብ.jpg

ድረ ገፁ አሁን በተመልካቾች ሪፖርት የተደረጉ ቪዲዮዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ሊታዩ አይችሉም ነው ያለው።

በዚህም የዕድሜ ገደብ ያላቸው ቪዲዮዎች በዩ ትዩብ ለልጆች መተግበሪያ ውስጥ እንዳይታዩ ታግደዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ሰዎች በአዋቂ መለያ ካልገቡ በስተቀር በጣብያው ድር ገፅ ላይ ማየት አይችሉም ነው የተባለው።

ሆኖም ተመልካቾች ሪፖርት ባለማድረጋቸው የተነሳ ብዙዎቹ ቪዲዮዎች አሁንም መታየት መቀጠላቸው ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ