በ5G ኔትዎርክ የሚሰራው የዓለማችን የመጀመሪያው ስማርት ስልክ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች 5ኛው ትውልድ (5G) የሚባለውን ኔትዎርክ ለመስራት በመሽቀዳደም ላይ ግኛሉ።

ብዙ ኩባንያዎች ይህን ኔትዎርክ እውን ለማድረግ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮቸን ኢንቨስት በማድረግ እየሰሩ ሲሆን፥ ኳል ኮም እና ኖኪያም ከእነዚህ ወስጥ ቀዳሚውን ሰፍራ ይይዛሉ።

በዚህ የወር መግቢያ አካባቢ ላይም ኳል ኮም በ5ጂ ኔትዎርክ የሚሰራ X50 የተባለ ሞዴም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች ደግሞ የኳል ኮም ኩባንያ በ5ኛው ትውልድ (5G) ኔትዎርክ የሚሰራ ስማርት ስልክ መስራቱ ተነግሯል።

የኳል ኮም ኤል.ቲ.ኢ እና 5ጂ ሞዴሞችን የሚሸጠው ሸሪፍ ሃና የተባለ የትዊተር ተጠቃሚ በገጹ ላይ የስማርት ስልኩም ምስል የለቀቀ ሲሆን፥ የመጀመሪያው የ5ጂ ኔትዎርክ ስማርት ስልክ ነው እያለም ይገኛል።

qualcomm_2.jpg

ስማርት ስልኩ ሁለት የጀርባ ካሜራዎች ያሉት ሲሆን፥ ፎቶ ግራፍ በጥራት ለማንሳት የሚያስችለው ኤል.ኢ.ዲ የፍላሽ ብርሃን እና የኳል ኮም አርማ ከጀርባው አለው ተብሏል።

ስማርት ስልኩ የኩባንያው የ5ጂ ስማርት ስልክ የመጨረሻው ዲዛይን አይደለም የተባለ ሲሆን፥ ኩባንያው ስልኩን በቅርቡ አጠናቆ ይፋ እንደሚያደርግ ነው እየተነገረ ያለው።

 

ምንጭ፦ fossbytes.com