ዜድ ቲ ኢ አራት ካሜራዎች ያሉት አዲስ የስልክ ምርትን ለገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዜድ.ቲ.ኢ. ሁለት አዳዲስ ኑቢያ የሞባይል ስልኮችን ዛሬ በቻይና ገበያ አስተዋውቋል።

ኩባንያው ኑቢያ Z17S እና ኑብያ Z17 የተሰኙ በቦርዳቸው ውስጥ አራት ካሜራዎች የተገጠሙላቸው ዘመናዊ ስልኮችን ነው ይፋ ያደረገው። 

የሞባይል ስልኮቹ 5 ነጥብ 73 ኢንች ስክሪን ስፋት ያላቸው ሲሆን፥ በቅርቡ ወደ ገበያ ይገባሉ ተብሏል።

ኑቢያ Z17S ስድስት ጂቢ ራም እና 64 ጂቢ የውስጥ አቅም ያለው ሲሆን፥ ዋጋው 455 ነጥብ 95 የአሜሪካን ዶላር ገደማ ነው።

ስምንት ጂቢ ራም እና 128 ጂቢ የውስጥ አቅም ያለው ኑቢያ Z17S ደግሞ ዋጋው እስከ 607 የአሜሪካን ዶላር እንደሚደርስ ተነግሯል።

ሁለቱም የኑቢያ ሞባይል ስልኮች ባለሁለት ባንድ ዋይፋይ (WiFi) እንደተገጠመላቸውም ኩባንያው አስታውቋል።

በተጨማሪም 3 ሸህ 200 ሚሊአምፒር ሰዓት አቅም ያለው ባትሪ የተገጠመላቸው መሆኑም ተገልጿል።

 

 

 

ምንጭ፦ ኢንድያን ኤክስፕረስ